ኢትዮጵያ በቱርክ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት በማህበራዊ መስክ ማጠናከር ትሻለች- ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2006 (ዋኢማ) - ኢትዮጵያ በቱርክ መካከል ያለው መልካም የኢኮኖሚ ግንኙነት በማህበራዊና በባህል ልውውጥ መስክም ማጠናከር እንደምትሻ የኢፌድሬ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዛሬ በኢትዮጵያ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የቱርክ አምባሳደርን ኡጉር ከናን በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው አሰናብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያለው ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንኙነት ወደ ሌሎች ግንኙነት መስክ ሊያድግ ይገባል።

ይህንኑ ግንኙነት ወደ ማህበራዊና ባህላዊ ግንኙነት ወደ ሌሎች መስኮች ከፍ ለማድረግ ኢትዮጵያ ፈላጎት እንዳላት ገልፀው በቱርክ በኩል ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በቆዩበት ጊዜ በሰሩት ውጤታማ ሥራም ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ አመስግነዋል።

አምባሳደርን ኡጉር ከናን በበኩላቸው እንዳሉት የቱርክ ባለሀብቶች በተለይ ካለፈው አስር ዓመት ወዲህ በኢትዮጵያ በስፋት በልዩ ልዩ መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

አምባሳደሩም በኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በላይ ቆይታቸውም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የህዝብ ለህዝብና የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ለማጠናከር በርካታና ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

ይህንኑ ግንኙነት ወደ ማህበራዊና ባህላዊ ግንኙነት አልፎም ወደሌሎች ግንኙነት መስኮች ከፍ ለማድረግ በቱርክ በኩል ፍላጎት መኖሩን ገልፀዋል።

እሳቸውም አምባሳደር ሆነው በሄዱበት ሁሉ ስለ ለኢትዮጵያ መልካም አገልግሎት ሁሉ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።