ወጣቱ ትውልድ ድህነትን ለማስወገድ ሊታገል ይገባል

  • PDF

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2005(ዋኢማ) - የቀድሞው ትውልድ የሀገሪቱ ነጻነት ተጠብቆ እንዲቆይ በማድረግ የፈጸመውን ጀግንነ ወጣቱ ድህነትን በማስወገድ ሊደግመው እንደሚገባ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት አሳሰቡ።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በነገው ዕለት ታስቦ የሚውለውን 74ኛውን የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ወጣቱ ትውልድ በተለይም የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ እውን በማድረግ ሀገሪቱን ከድህነት ማውጣት ይጠበቅበታል።

በነገው እለት ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት በሚካሄደው ስነ-ስርዓት ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናትና ተማሪዎች እንደሚገኙ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

በዕለቱ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት፣ የእንግዶች መልዕክትና ሌሎች ዝግጅቶች   እንደሚኖሩ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ገለጻ በቅድስት ስላሴ ካቴዴራል ቤተክርስትያንና በአንዋር መስጊድ የጸሎት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድም የማህበሩ ፕሬዝዳንት መግለፃቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።