የኢፌዲሪ መከላከያ ቀን በአል የሰራዊቱ ህገመንግስታዊነትና ህዝባዊነት ይበልጥ የሚጎለብትበት መሆኑ ተገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ ጥር 30/2005 (ዋኢማ) -የመከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ህገመንግስታዊነትና ህዝባዊነቱ ይበልጥ የሚጎለብትበት መሆኑን የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ ገለፁ፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ የምስራቅ ዕዝ አባላት የሰራዊት ቀን በዓልን በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ማክበር ጀምረዋል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ በአነስተኛ ወጪና በአጭር ጊዜ የግዳጅ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የዕዙ መዋቅሮችና አባላት፣ ለሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና ክልሎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል አብርሃ ወልደማርያም ሰራዊቱ በሶማሌ ክልል የፀረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍ ከህዝቡ እንዲነጠሉ ማድረግ ችሏል ብለዋል፡፡
በዚህም ክልሉን የልማት ቀጠና ማድረግ መቻሉን ጀነራል ሳሞራ ተናግረዋል ፡፡ (ኢሬቴድ)