ባለሃብቶቻችን በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥረት እናደርጋለን” የጀርመን የፓርላማ አባላት

  • PDF

አዲስ አበባ ጥር 29/2005 (ዋኢማ) - ጀርመናውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ተጠቅመው በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ጥረት እንደሚያደርጉ የጀርመን የፓርላማ አባላት ገለጹ፡፡

የጀርመን ፓርላማ የበጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እያከናወነች ያለችውን ተግባራት ለፓርላማ አባላቱ አብራርተዋል፡፡

በጀርመን ፓርላማ የበጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሀርበርት ፍራክሀውስር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት እና ለአፍሪካ ሰላም እና መረጋጋት እያከናወነች ያለችውን ጥረት እንደሚያደንቁ ተናግረዋል፡፡

ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል የፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል፡፡(ኢሬቴድ)