በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የ2.5 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ግዢ ፈፀሙ

  • PDF

አዲስ አበባ ጥር 29/2005 (ዋኢማ) - በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 2.5 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ግዢ ፈጸሙ፡፡

ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ቃል ተገብቷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫልና የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት የ2ኛ አመት በዓል በአቡዳቢ ተከብሯል፡፡

በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የኢፌዲሪ ቆንስላ ጀነራል አቶ ምስጋኑ አረጋ እንዳሉት በአካባቢው ያሉ ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ለልማታችንና ዕድገታችን ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ቦንድ በመግዛትና ቃል በመግባት ያሳዩት ተሳትፎ ለሌላውም በአርአያነት የሚጠቀስ ከመሆኑም ባሻገር ግድቡን በእርግጥም በእራሳችን አቅም መገንባት የምንችል መሆኑን ያረጋገጠ ነው፡፡

በህዝባችን ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ይህ ከፍተኛ መነሳሳት ህዝቡ ከድህነት ለመላቀቅ ያለውን ፅኑ ፍላጎት የሚያመላክትም ነው ብለዋል አቶ ምስጋኑ፡፡ (ኢሬቴድ)