ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች ቃል ከገቡት ውስጥ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተሰበሰበ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2005(ዋኢማ) - ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ቃል ከተገባው  11 ቢሊየን 127 ሚሊየን ብር  ከመንግስትና ከግል ተቋማት ሰራተኞች ብቻ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ።

የመንግስትና የግል ተቋማት ሰራተኞች ቃል ከገቡትን 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ሙሉ በሙሉ የተሰበሰበ ሆን፤ የሁለተኛ ዙር የቦንድ ግዥ መጀመራቸውንም በጽህፈት ቤቱ የሚዲያና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ከተማ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቃል ከተገባው 11 ቢሊየን ብር 127 ሚሊየን ብር ውስጥ እስከ አሁን 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የሚሆነዉ ተሰብስቧል ብለዋል፡፡
ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ግድቡ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አዳዲስ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሎተሪ ዕጣና ትላልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ማዘጋጀት ከገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶቹ መካከል ይገኙበታል፡፡
እንዲሁም ከአጭር የስልክ የጽሁፍ መልዕክት 1 ቢለዮን ብር ለመሰብሰብ በእቅድ ተናግረዋል።

እስከ ታህሳስ 2005 ዓ.ም የግድቡ ግንባታ 14 ነጥብ 1 በመቶ የተከናወነ ሲሆን፤ በአመቱ መጨረሻም 26 በመቶ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።