ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በአካባቢ ጥበቃና በኢንቨስትመንት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተሰማሙ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ጥር 23 /2005 (ዋኢማ) - ፈረንሳይ በአካባቢ ጥበቃ እና በኢንቨስትመንት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት እንደምትፈልግ ገለፀች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውረን ፋቢያስ የተመራውን የልዑካን ቡድን በትናንትናው ዕለት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት የኢትዮ -ፈረንሳይ የቆየ ግንኙነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አክለውም በሁለቱ ሀገሮች ያለው ታሪካዊ ግንኙነት ረጅም ጊዜ የቆየ ቢሆንም የፈረንሳይ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋለነዋያቸውን በማፍሰስ ረገድ ያለው እንቅስቃሴው አነስተኛ ስለሆነ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውረስ ፋቢያስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችውን አሰተዋጽኦ አድንቀው በአካባቢ ጥበቃ ላይም ከሀገራቸው ጋር በትብብር እንድትሰራ መጠየቃቸውንም የኢሬቴድ ዘግቧል።