በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በድምቀት እየተካሄደ ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2005(ዋኢማ) - በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከትናንት በስቲያ ተጀምሯል።

በመክፈቻውም ባደረገቻቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች አሳማኝ ቡድን ይዛ አልቀረበችም በሚል በደጋፊዎች ተቃውሞን እያስተናገደች ያለችው አስተናጋጇ ደቡብ አፍሪካና ኬፕ ቨርዴ ተጫውተው ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል።

በዚሁ ምድብ አንድ የሚገኙት ሞሮኮና አንጎላ ምሽት 4 ሰአት ላይ ተገናኝተው ዜሮ ለዜሮ ነው የተለያዩት።

እሁድ እለት በቅድሚያ የተገናኙት ጋናና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ 2 ለ 2 ሲለያዩ፥ ማሊ ኒጀርን ባለቀ ሰአት ሰኢዱ ኪታ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ማሸነፍ ችላለች።

በዛሬው ዕለትም ምሽት 12 ሰዓት በሶስተኛው ምድብ የተመደቡት ኢትዮጵያ ከዛንቢያ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፤ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ናይጄሪያ ከቡርኪናፋሶ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።