የዋሊያዎቹ ሽኝት

  • PDF

አዲስ አባባ፤ ጥር 6/2005 (ዋኢማ) - ለዋሊያዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ማምሻውን የሽኝት ሥነስርአት ተከናውኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ሥነሥርአት ላይ ተገኝተው የኢትዮያን ሰንደቅ ዓላማ ለቡድኑ አምበል ደጉ ደበበ በአደራ አስረክበዋል።

በጨዋነት የአገራችሁን ስም ለማስጠራትና የምትችሉትን ውጤት ለማምጣት እንድትጥሩ አደራ እላለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ።

በሥነሥርአቱ ላይ ሼህ ሞሐመድ አላሙዲን ለወንዶቹ ቡድን ለዋሊያዎቹና ለሴቶቹ ቡድን ሉሲዎች የሰጡት 10 ሚሊየን ብር ሽልማት ለየቡድኖቹ አባላት ተበርክቷል።

ምሽቱንም ለኢትዮያ ብሔራዊ ቡድን አባላት በአሜሪካ ከተሰሩት ቱታዎች አንዱን ለጨረታ በማቅረብና ሌሎችም ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች ተካሂደዋል። ለቡድኑ ገቢ ለማስገኘት ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም የስፖርት ፌስቲቫል ይካሄዳል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በዚሁ ፌስቲቫል ገበናና ሰው ለሰው የተሰኙት የቴሌቪዥን ድራማዎች ተዋንያን የሚያደርጉት የእግር ኳስ ግጥሚያ ይገኝበታል።