የታላላቆቹ ሐይቆች አካባቢ አገራት ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2005 (ዋኢማ) - የታላላቆቹ ሐይቆች አካባቢ አገራት የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮች በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጉዳይ ላይ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ አካሄዱ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው የሚኒስትሮቹን ስብሰባ የመሩት የአፍሪካ ኅብረት የሠላምና ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ራምታኔ ላማምራ ናቸው፡፡

በስብሰባው ላይ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ /ሳዴክ/፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ረመንግሥታት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብና የታላላቆቹ ሐይቆች አካባቢ አገራት ዓለም ዓቀፍ ጉባዔ ተወካዮችና የሌሎችም ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች መሳተፋቸውን ገልጿል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ ስብሰባው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል ገለልተኛ ዓለም ዓቀፍ ኃይል በሚሰማራበት ሁኔታ ላይ መምከሩን ጠቁሟል፡፡