የአፍሪካ ኅብረት የሠላምና ፀጥታ ኮሚሽነር በሩዋንዳና በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፓብሊክ ጉብኝት ሊያካሂዱ ነው

  • PDF

አዲሰ አበባ፤ ታሀሳሰ 25/2005ዋአኢማ) - በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሠላምና ፀጥታ ኮሚሸነር አምባሳደር ራመታኔ ላማምራ የሚመራ ቡድን በጥር ወር መግቢያ ላይ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፓብሊክና በሩዋንዳ የአራት ቀናት የሥራ ጉበኝት እንደሚያደርጉ የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እንዳስታወቀው በኮሚሽነሩ የሚመራ የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣናው ሠላምና መረጋጋት በሚጠናከርበት ዙሪያ ይመክራል፡፡

ቡድኑ በኪጋሊ ቆይታው ሩዋንዳ የኅብረቱ የሠላምና ፀጥታ ኮሚሽን አጀንዳዎችን መደገፍ በምትችልበት ሁኔታ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡