የአዲስ አበባና የኒው ዴልሂ ከተሞች ግንኙነት መመስረቻ ስምምነት ተፈራረሙ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2005(ዋኢማ) - በአዲስ አበባና ኒውዴልሂ ከተሞች መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የእህትማማች ግንኙነት የሚመሰርትበት የፕሮቶኮል ስምምነት መፈረሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በሕንድ ኒውዴልሂ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

ስምምነቱን የተፈራራሙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና የሰሜን ኒውደልሂ ከተማ ከንቲባ ሚስ ሚራ አግራዋ ናቸው፡፡

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት ከተሞች መካከል በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በጤና፣ በፓርኮች ልማትና አካባቢ ጥበቃ ዘርፎች እንዲሁም በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያስችላል፡፡
ሚስ አግራዋ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ ኩማ የኒውዴልሂ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ ከሚስ ሸይላ ዲክሽትን ጋር አዲስ አበባ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም አመቺነት በመግለጽ እንዲጎበኟት መጋበዛቸውን የኤፍቢሲ  ዘገባ ያስረዳል።