ብዙህነትን ማስተናገድ ተስኗት ስትንገዳገድ የኖረች አገር

  • PDF

ዮናስ
በአገራችን በየአመቱ የምናከብረው የዘመን መለወጫ በዓል ሲመጣ ከሰፈር ጓዳኞቼ ጋር የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተን እንከራከር ነበረ፡፡አከራካሪ ጉዳይ የነበረውም የዘመን መለወጫ የሚባለው ነው ፡፡ሁለት ሺህ አምስት ዓመታት ሲቀያየሩ እንጂ ዘመን ሲለወጥ ስላላየን ነው፡፡ ሁለት ሺህ ዓመታት ስለተተካኩ ብቻ ዘመን ተለውጧል ማለት አንችልም፡፡ በርግጥ ዘመን ተለውጧል የUንለው የመጠን ሳይሆን የዓይነት ለውጥ ሲኖር ነው፡፡ የዓይነት ለውጥ ሳይኖር እንዴት ዘመን መለወጫ ሊባል ይችላል; የሚሉት ጉዳዮች   ነበሩ የሚያከራክሩን፡፡ አሁን ቆም ብለን ስናስብ በርግØም ክርክራችን ስህተት አልነበረም፣ መነሳት ያለበት ጉዳይ  ነው፡፡

ይህን ያስታወሰኝና ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በነጻ አስተያየት የአዲስ አድማስ መድረክ ላይ ታህሳስ 13 የተወሳውና ዛሬም ወደኋላ የሚያስበው አጀንዳ ነው።
ያለፉትን ሁለት ሺህ ዓመታት የአገራችን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን ስንቃኝ ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ጎልተው ይታያሉ፡፡
በመጀመሪያው ሺህ ዓመት አገራችን በስልጣኔ በመጀመሪያው ረድፍ ከሚገኙ የአለም አገሮች መካከል ነበረች፡፡በሁለተኛው ሺህ ዓመት የመጀመሪያው አጋማሽም ከመጀመሪያው ረድፍ ብዙም ሳትርቅ ብትቆይም፣ በሁለተኛው ሺህ ሁለተኛ አጋማሽ ግን በማያቋርጥ የማሽቆልቆል ሂደት ውስጥ ተዘፍቃ በአለም ደረጃ የድህነትና የተመፅዋችነት ተምሳሌት የምንሆንበት ደረጃ ላይ ደርሰን በመጨረሻም በስልጣኔ የአገሮች ጭራ የሆንበት ሂደት መኖሩን ከታሪካችን እንገነዘባለን፡፡በሁለት ሺህ ዓመታት ውስጥ ሁለቱንም የዕድገት ጫፎች መቅመሳችንን ታሪካችን በማያሻማ መልኩ ያረጋግጥልናል፡፡

ለዕድገቱም ሆነ ለውድቀቱ የታሪክ ተመራማሪዎች የየራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸው እኔ ግን    የአገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ወደጎን ትተን ከውß አምØተን እንዳለ የምንተገብረው ጉዳይ ይመስለኛል ችግራችን፡፡ ለምሳሌ ስለ ሃይማኖት መከባበርና መቻቻል ከሌላ የምንማረው ብዙ ነገር ያለ አይመስለም፡፡
ከሃይማኖት ብዙህነት አኳያ ያለውን ጉዳይ ብናይ አገራችን ከመካከለኛው ምስራቅ የመነጩትን  ሁለት ሃይማኖቶች ማለትም  ፣ክርስትናን እና እስልምናን ከተቀረው የዓለም ክፍል አስቀድማ የተቀበለች አገር ስለመሆኗ ምንም አከራካሪ ጉዳይ የለም፡፡ በታሪካችን ውስØ አልፎ አልፎ ሃይማኖታዊ ገፅታ የነበራቸው ግጭቶች እንደነበሩ የማይካድ ቢሆንም፣ እነዚህ ሃይማኖቶች ለረጅም ጊዜ ተከባብረው በሰላም አብረው መኖራቸው ደግሞ የታሪካችን ገፅታ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት አገራችን የአንድ ሃይማኖት አገር ሆና እንደማታውቅ ማስቀመØ ይቻላል፡፡

የሃይማኖት ታሪኳም ሲቃኝ የብዙህነትን ታሪክ ነው የሚያሳየው፡፡  የሃይማኖት እኩልነትን ስናነሳ  በአፄ ሃይለ ስላሴ ዘመን የሃይማኖት መቻቻል እንደተጠበቀ ሆኖ የኦርቶዶክስ ክርስትና የመንግስት ሃይማኖት የሆነበት፤በደርግ መንግስት ደግሞ መንግስትና ሃይማኖት ተለያይቷል ቢባልም ሁሉም ኃይማኖቶች በተለያየ ደረጃ የተረገጡበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡

በሌላ በኩል አገራችን በነበሩ በተለያዩ የአካባቢ መንግስታት የተለያዩ ቋንቋዎች፣ባህሎች ወዘተ ያላቸው ብሄረሰቦች እንደነበሩ ታሪክ ያረጋግጣል፡፡በእያንዳንዱ መንግስት አስተዳደር ስር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአካባቢ መንግስታት አስተዳደር ስር የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ሲኖሩ እንደነበርም ግልፅ ነው፡፡

ይህ  ጉዳይ እንዳለ ከዘመነ መሳፍንት እስከ አፄ ምኒልክ ድረስ ከ150 አመታት ላላነሰ ጊዜ ቀØሎ የኢትዮåያ ድንበር የአሁኑን መልክ እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ዘልቋል፡፡ ነገስታቱ አንድነትን በመፍÖራቸው ይመሰገናሉ፡፡ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተÖቀሙበትን መንገድ ስናይ ደግሞ  የታሪክ ተወቃሾች ናቸው፡፡ብዙህነትን ማስተናገድ አቅቷት ለመውደቅ ስትንገዳድ፣፣ ስትወ× ስትወርድ የቆየችው አገራችን እጅግ አሰገራሚ በሆነ ሁኔታ በተፈÖረው አንድነት ነፃነቷን Öብቃ ቆይታለች፡፡ ከልማት፣ከዴሞክራሲ ፣ ከሰላም እና ከብዙህነት Øያቄ  አኳያ ደግሞ  ምድረበዳ ሆና ኖራለች፡፡ ዳገት መው×ት የተሳነው ዘመናዊው የዘውድ አገዛዝ ስሙ ተቀይሮ እስከ ደርግ መንግስት ቀØሎ ህብረብሄራዊ ብዙህነትን እንደ ድክመት በመውሰድ በቀረፁት አንድ ወØ ኢትዮåያዊነት  ከጭቆናና ድህነት ጋር ለዘመናት እንድንኖር አድርጎናል ፡፡ይህ ፖሊሲ የßቁን ብሄር ብሄረሰቦችን ተቃውሞና አመፅ መጋበዙ አልቀረም፡፡የገበሬዎች አመጽ እና የተማሪዎች የዴሞክራሲ ትግልንም መቀስቀሱ አልቀረም፡፡ብዙዎች በኢትዮåያ አንድነት ስም ተÚፍßፈዋል፤ከአገር ተሰደዋል፡፡ሚሊዮኖች በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል፡፡ይሁን እንጂ አንድ ቀን Úለማው መገፈፉ  እንደማይቀር ይታወቃልና የግንቦት 20 ፀሃይ   ፈነÖቀች፡፡

ባይተዋር የነበሩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁሉ ተሰበሰቡ፣ያን የተዛባ ታሪክ ለመቀየር ምሁራን ቁጭ ብለው መፍትሄ በማፈላለግ በፍላጎት የተመሰረተ አንድነት መፍጠር አለብን አሉ፡፡ የተለያዩ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አንግበውት የተነሱትን የብሄር ጥያቄ በጥንቃቄ በመለየት በአገራችን ዳግም የብሄር ጭቆና እንዳይመለስ ሁሉም እኩል የሆኑበት አገር ለመፍጠር ቆርÖው ተነሱ ፡፡ ይህንንም በህገ መንግስቱ መግቢያ እንዲህ ብለው አሰፈሩ ፡-

" እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦች ህዝቦች በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ፣ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታችን እንዲፋጠን፣የራሳችንን ዕድል በራሳችን የመወሰን መብታችንን ተጠቅመን ፣በነፃ ፍለጎታችን በህግ የበላይነትና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት፣ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የግለሰብና የብሄር ብሄረሰብ መሠረታዊ መብቶች መከበራቸው፣ የፆታ እኩልነት መረጋገጡ፣ባህሎችና ሃይማኖቶች ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረጉ እሰፈላጊነት ፅኑ እምነታችን በመሆኑ፣ኢትዮጵያ አገራችን የየራሳችን አኩሪ ባህል ያለን፣የየራሳችን መልክአ ምድር አሰፋፈር የነበረንና ያለን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት አገር በመሆኗ ያፈራነው የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፣መጭው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል፣...በማለት
ረቂቁ ለህዝብ ውይይት ቀረበ በውይይትም ዳበረ፣ በመረ×ቸው ወኪሎቹ  አማካነት የውል ስምምነት ሆኖም ፀደቀ ፡፡

ህገ-መንግስቱ ውስØ የአገራችንን ተÚባß ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የግለሰብና የጋራ መብቶች በእኩል እንዲከበሩ ህገ መንግስታዊ ሙሉ ጥበቃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ሆኖም የጋራ መብቶች መከበር የግለሰብ መብት እንዲረገጥ ያደርጋል ፤ከሁለቱ መብቶች የበላይነት የሚሰጠው ለማነው; ወይም በጣም አስፈላጊ መብት የቱ ነው; የሚሉ ወገኖች አልጠፉም። ህገመንግስቱ ግን መብቶቹን በተናጠል ሳይሆን አጣምሮ ነው ያያቸው፡፡ በፍልስፍና ደረጃ መከራከር ይቻላል፡፡ነገር ግን በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ የግለሰብና የጋራ መብቶች ተነጣጥለው ሊታዩ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በኛ አገር ሁኔታ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተሟላ መልኩ ሳይከበር የግለሰቦች መብት ማስከበር አይቻልምና ነው።በተመሳሳይ መልኩ ሃሳብን በራስ ቋንቋ በነፃነት የመግለፅ፣በመሰላቸው አኳኋን እንዳይደራጁ መከልከል፣የመብቶች ሁሉ አናት የሆነው በሕይወት የመኖር መብት ሳይከበር የጋራ መብቶችን ማስከበር ስለማይቻል ነው፡፡ በሕይወት ያለ ሰው ነው ከሌሎች ጋር መደራጀት የሚችለው፡፡ በሌላ አገላለፅ የግለሰብ መብት ለጋራ መብቶች መሠረት ነው፡፡ ሁለቱም መብቶች ተሳስረው እንዱ ለሌላው መከበር መሠረት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ህገ መንግስቱ የግለሰብን መብት በማስከበር ሽፋን የጋራ መብቶችን መጣስን እንደማይፈቅድ ሁሉ የጋራ መብቶችን በማስከበር ሽፋንም የግለሰብ መብትን አይጥስም።
በህገመንግስቱ አንቀፅ 25 ላይ እንደተቀመጠው በመካከላቸው ምንም ልዩነት ሳይኖር ዕኩል ጥበቃ ያደርግላቸዋል፡፡
ይህም በመሳካቱ  የልማት ፣የዴሞክራሲ እና የሰላም ምድረበዳ የነበረችው አገር የልማት፣የዴሞክራሲ እና የሰላም ለም አፈር ሆናለች፡፡ህዝቡ  ነፃነት በማግኘቱም አይደል ልማቱ የተፋጠነው?
ከሰብዓዊ መብት አንፃር ብናይ በአለም ዓቀፍ ደረጃ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስትነቀፍ የነበረችው አገር ዛሬ ግን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አባል መሆኗ ከምን የመጣ ይመስለናል; በተግባር በተገኘ ውጤት አይደለምን?ሌላው ቀርቶ አገሪቷ  በድህነት ወለል ላይ ወድቃ ማን ደረሰላት። በኦክስ ፎርድ መዝገበ ቃላት ላይ የ’Famine’ ወይም የረሐብ  ተምሳሌትነቷ     የተፋቀው በወሬ ሳይሆን በብሄር ብሄረሰቦች ተጨባጭ ተግባር ነው፡፡ 
ከሰብአዊ መብት አያያዝ አንፃር የአገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ በማስታወስ ኢህአዴግን ከደርግ ጋር  በማወዳደር ብዙ ነገር ማንሳት ይቻላል፡፡ነገር ግን በአይነትም በመጠንም የማይገናኘውን አብሮ ማወዳደር ትዝብት ነውና ልለፈው፡፡

አንዳንድ ፀሐፊዎች “ኢህአዴግ ለግለሰብ ነፃነት መከበር አይጨነቅም ለቡድን መብት ነው የሚጨነቀው” ፡፡ “ኢህአዴግ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ ነው።” ከሚል “ምን አለበት የግለሰብ ነፃነት ለኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ ነውቢል” ይላሉ፡፡
የህገመንግስቱን ምዕራፍ 13 ከአንቀፅ14 እሰከ 44 ያሉትን በማየት ከአለም ሰብኣዊ መብቶች ስምምነት ጋር ቢያነፃፅሩት ጥያቄውን ማንሳት አስፈላጊ እንዳልነበር በተገነዘቡ፡፡
በሌላ በኩል“የሌሎችን ሕይወት እንዳሻው የማዘዝ ስልጣን የያዘ አካል አለ ብለው የሚያምኑም አሉ፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ህገ መንግስቱ ገደብ ያልጣለበት ስልጣን የያዘ አካል አለ ማለት ተጠያቂነት የሌለው ከብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሉኣላዊነት በላይ የሆነ አካል አለ ማለት ከሆነ እኔ አላውቅም፡፡መገለጫውን ቢያስቀምጡ ለመቀበልም ለመከራከርም ጥሩ ነበር፡፡ሌላ ቀርቶ ዛሬ አንድ አባወራ በገዛ ቤተሰቡ አባላት ሕይወት ላይ አንዳሻው ማዘዝ አይችልም፡፡ሌላው ደግሞ  ከኪራይ ሰብሳቢዎች ትርምስ ተነስተው ኢትዮጵያ ላይ ላዩን ስትታይ የተረጋጋች ሰላማዊ አገር ትመስላለች ነገር ግን በቀላሉ ልትቃወስ የምትችል አገር ነች በማለት የሚፅፉት የእነርሱን ቀውስ ወደ አገር ቤት አምጥቶ ማንም ጆሮ በማይሰÖው ወሬ መሞኘት ብልህነት ሳይሆን ጅልነት ነው።ፀሐፊው ኢትዮጵያን ይወዳል ግን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦቿንና ህዝቦቿን አይደለም ግዛቷን እንጂ፡፡የሚወደው በምድሯ ላይ የተፈጠሩትን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦቿን አይደለም፡፡ራሱን ነው የሚወደው፡፡ለዚህ ነው ብጥብጥና ቀውስን የሚመኝላት፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ፀሐፊው ይፈጠራል የሚለውን ቀውስና ብጥብጥ በመተው ለአገር እድገትና ብልፅግና ቀናውን ነገር ቢያስብ ለራሱ የማይፈልገውን ለሌላ ባይመኝ፡፡ይልቁንም ታሪክ እየሰራ ካለው ትውልድ ጋር ቢቀላቀል መልካም ነው  ።