የኢትዮጵያ መንግሥት ለጎረቤት አገራት ስደተኞች ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች መሆኑ ተገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2005 (ዋኢማ) - የኢትዮጵያ መንግሥት ለጎረቤት አገራት ስደተኞች እያደረገ ያለው አቀባበልና አያያዝ ለሌሎች አገራት አርአያ መሆኑን በኢትዮጵያ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ተወካይ ገለጹ፡፡

ሚስተር ሞከስ ኤኬሎ በትግራይ ክልል በፀለምት ወረዳ የሚገኙ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች በጎበኙት እንደገለጹት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከ370 ሺህ በላይ የኤርትራ፣ የሶማሊያና ሱዳን ስደተኞች በማስተናገድ ላይ ትገኛለች፡፡

ስደተኞቹ ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ የምግብና ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የትምህርት ዕድል ተመቻችቶላቸው ሰላማዊ ኑሮ እየኖሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ ሁሉም ስደተኞች መንግሥት እያደረገ በሚገኘው ድጋፍ ደስተኞች በመሆናቸው ኢትዮጵያ ሁለተኛ አገራቸው እንደሆነች እንደሚያስቡም ተናግረዋል፡፡