የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የሰላም ጉዳይ ላይ መከሩ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 16/2005 (ዋኢማ) -   በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለመፍታት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሁለቱም ክልሎች አዋሳኝ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የሰላም ጉዳይ ላይ በሞያሌ መክረዋል፡፡ አለመግባባቶችን ለመፍታትም የደረስንበትን ስምምነት እናከብራለን ብለዋል፡፡

በኢትዮ ኬንያ የድንበር ከተማ ሞያሌ የተካሄደው የሰላም ጉባኤ በተለይ ባለፈው አመት ሀምሌ ለተፈጠረው አለመግባባት መንስኤዎች መለየትና በአካባቢው ሰላም ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው::

የጉባኤው ተሳታፊ አባገዳዎች፣ ኡጋዞችና የአካባቢው ነዋሪዎች በከተማው አንዳንድ ቀበሌዎች ላይ የሚነሳ የይገባƒል ጥያቄ ፣ የጎሰኝነት አመለካከት ፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የፀረ ሰላም ሃይሎች ጣልቃ ገብነትን ላለማግባባቱ በምክንያትነት አንስተዋል::

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው እንዳሉት በሞያሌ ከተማ ተከሰቶ ለነበረው አለመግባባት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ የአካባቢው አመራሮችና ሌሎችም አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል::

በከተማው በአንዳንድ ቀበሌዎች ላይ የሚነሳው የይገባƒል ጥያቄ ለተፈጠረው አለመግባባት መንስኤ መሆን እንደማይገባውና ለጥያቄው መንግስት መፍትሄ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል:: "የሰላም ዋናው ዋስትና ዘላቂ ልማት ማምጣት ነው፡፡ ወደ ልማት የገባ ህዝብ የሰላም ሃይል ይሆናል፡፡ የመንግስት ሃላፊነት አንዱ በአርብቶ አደር አካባቢ የጀመራቸው የልማት ስራዎች ማቀላጠፍ ይሆናል::ሁለተƒ ግጭቶች የሰው ህይወት መቅጠፍ ድረስ ከመድረሳቸው በፊት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርአት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡”

የጉባኤው ተሳታፊዎች በአካባቢያቸው  የሚከሰት አለመግባባትን በባህላዊ እርቅ ለመፍታት ከአሁን ቀደም ነጌሌ ላይ የደረሱበትን ስምምነት ባለመተግበራቸው ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት አለመቻላቸውንና አሁን ግን ስምምነቱን መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል::

"በጉጂ ዞን ነጌሌ ላይ ተወያይተን አለመግባባቶች ሲከሰቱ በባህላዊ መንገድ ለመፍታት የደረስንበትን ስምምነት በመተግበር ችግሮችን በእንጭጩ መቅጨት አለብን በእƒ መካከል አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በተመለከተ ቃል የምንገባው ችግሮች ሲከሰቱ በሰላማዊ መንገድ ተፈተው በልማት መስክ የሚጠበቅብንን እንደምንወጣ ነው::"

እንደ ኢዜአ ዘገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድና የሶማሌ ክልል አፈ ጉባኤ አቶ መሀመድ ረሺድ በበኩላቸው የአካባቢውን አርብቶ አደሮች የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ጥረት ይደረጋል ብለዋል::

ሁለቱ ክልሎች አንዱ የሌላውን መልካም ተሞክሮ የሚቀስሙበት መድረክ ይመቻቻልም ብለዋል::በመጨረሻም ለሁለት ቀናት የተካሄደው የሰላም ጉባኤ ተሳታፊዎች የተጀመሩ የሰላም የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ቃል በመግባት ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርአት አካሂደዋል::