ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 7 ሚሊየን 600 ሺ ቤተሰቦችን በሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲታቀፉ ማደረጉ ተገለፀ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2005 (ዋኢማ) - ባለፈው የበጀት ዓመት ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር የነበረባቸው 7 ሚሊየን 600 ሺ ቤተሰቦች በሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲታቀፉ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ መሀመድ አባሚልኪ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለጹት፤ በፕሮግራሙ ለታቀፉት ቤተሰቦች የብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን በማቅረብ ከነበረባቸው ችግር እንዲላቀቁ ጥረት ተደርጓል።

በበጀት ዓመቱ በፕሮግራሙ እንዲታቀፉ ታቅዶ የነበረው ቤተሰቦች ቁጥር 3 ሚሊየን 700 ሺ እንደነበርም ኃላፊው ገልፀዋል፤ አፈፃፀሙ ግን ከእጥፍ በላይ እንደነበር ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው የነበሩ 226ሺ 881 አባወራዎችን ደግሞ ከፕሮግራሙ ማስመረቅ ተችሏል ብለዋል።

እንዲሁም 13ሺ 560 አባወራና እማወራዎችን ደግሞ የተሻለ ለምነት ባላቸው አካባቢዎች እንዲሰፍሩ መደረጉንም አቶ ሞሃመድ መናገራቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።