ኤ ኤን ሲ ጃኮብ ዙማን በድጋሚ መረጠ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2005/ (ዋኢማ) -  በደቡብ አፍሪካ  ገዢው የአፍሪካ  ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ  /ኤኤንሲ/  ፕሬዚዳንት  ጃኮብ ዙማን በድጋሚ መሪው አድርጎ መረጠ።

ከጃኮብ ዙማ  ጋር  እጩ ሆነው የቀረቡት የእሳቸው ምክትል የነበሩት ኪጋሌማ ሞትላንቴ የነበሩ ሲሆን፤ በትናንትናው ምርጫም ሲይሪል ራማፎሳ በምክትልነት ተመርጠዋል።

አራት ሺህ ተወካዮች  የተሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው  ኤኤንሲ በአብላጫ ድምፅ ነው ዙማን በመሪነት የመረጠው።

ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ  ኤኤንሲን ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት የሚመሩ  ሲሆን፤ በዚህም  መሰረት  እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር በ2014 በሚካሄደው ጠቅላላ  ምርጫ  ፓርቲያቸው አሸናፊ ከሆነ በፕሬዚዳንትነት መቀጠላቸውንም አረጋግጠዋል።

ከአፓርታይድ ፍፃሜ በኋላ ላለፉት 18 ዓመታት ደቡብ አፍሪካን የመራው ኤኤንሲ በቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ እንደሚያሸንፍ ከወዲሁ መገመቱን ቢቢሲ ዘግቧል።