የአፍሪካ ኀብረት 50ኛ የምሥረታ በዓል አከባበር በመጪው ጥር ወር ይጀመራል

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2005 (ዋኢማ) ¬ 50ኛ ዓመት የአፍሪካ ኀብረት የምሥረታ በዓል አከባበር ከጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ የሚጀመር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኀብረቱ የተመሠረተበትን የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር ለአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች ገለጻ ተደረገላቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና አማካሪና የአፍሪካ ኀብረት ምሥረታ 50ኛ ዓመት በዓል አከባበር ሴክሬታሪያትና ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መኮንን ሐዲስ እንዳሉት የበዓሉ አከባበር ከጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ይጀመራል።

ላለፉት 50 ዓመታት የቀድሞ አፍሪካ አንድነት ድርጅት እና የአሁኑ የአፍሪካ ኀብረት ሂደት እንዲሁም ለአህጉሩ ያበረከተው አስተዋጽኦ በዝርዝር የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል። ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ላይ የሚከበረው የአፍሪካ ኀብረት የምሥረታ በዓል ላይ የእግር ኳስ፣ የመረብና የቅርጫት ኳስ ውድድሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የግብጽ፣ የደቡብ አፍሪካና የናይጄሪያ አገሮች የእግር ኳስ ውድድር ለማካሄድ ፍላጎት እንዳላቸውም አመልክተዋል።

በዓሉ ከስፖርታዊ ውድድሮች በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፋሽን ትርዒቶች የሚቀርቡ ሲሆን ታዋቂ የኢትዮጵያ ሞዴሎች እንዲመሩት ይደረጋል ብለዋል። ዓለም አቀፍ ውይይቶችን ለማካሄድ የቢ ቢ ሲ እና የሲ ኤን ኤን መገናኛ ብዙኃን ጥያቄ ማቀረባቸውን ፕሮፌሰር መኮንን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሩ ያላቸው ራዕይና ለገጽታ ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በበዓሉ ላይ የሚቀርብ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የኀብረቱ 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አዘጋጅ አገር በመሆኗ ብቻ ልዩ ትርጉም የሚሰጣት ሳይሆን ቅኝ ግዢን ከአፍሪካ አህጉር ለማስወገድ ባደረገችው ግንባር ቀደምት ትግል ጭምር መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤምባሲዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካ ኀብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ፕሮፌሰር መኮንን ገልጸዋል።

እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር 1955 የቀድሞ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ከመሰረቱት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን የድርጅቱ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግላለች። የአፍሪካ ኀብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በመጪው ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ከተከበረ በኋላ ኢትዮጵያ ኀብረቱን በሊቀ መንበርነት ትመራለች።

ኀብረቱ የተመሠረተበትን የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር ለአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች ገለጻ ተደረገላቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና አማካሪና የአፍሪካ ኀብረት ምሥረታ 50ኛ ዓመት በዓል አከባበር ሴክሬታሪያትና ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መኮንን ሐዲስ እንዳሉት የበዓሉ አከባበር ከጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ይጀመራል።

ላለፉት 50 ዓመታት የቀድሞ አፍሪካ አንድነት ድርጅት እና የአሁኑ የአፍሪካ ኀብረት ሂደት እንዲሁም ለአህጉሩ ያበረከተው አስተዋጽኦ በዝርዝር የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል። ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ላይ የሚከበረው የአፍሪካ ኀብረት የምሥረታ በዓል ላይ የእግር ኳስ፣ የመረብና የቅርጫት ኳስ ውድድሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ጠቁመዋል። የግብጽ፣ የደቡብ አፍሪካና የናይጄሪያ አገሮች የእግር ኳስ ውድድር ለማካሄድ ፍላጎት እንዳላቸውም አመልክተዋል።

በዓሉ ከስፖርታዊ ውድድሮች በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፋሽን ትርዒቶች የሚቀርቡ ሲሆን ታዋቂ የኢትዮጵያ ሞዴሎች እንዲመሩት ይደረጋል ብለዋል። ዓለም አቀፍ ውይይቶችን ለማካሄድ የቢ ቢ ሲ እና የሲ ኤን ኤን መገናኛ ብዙኃን ጥያቄ ማቀረባቸውን ፕሮፌሰር መኮንን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሩ ያላቸው ራዕይና ለገጽታ ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በበዓሉ ላይ የሚቀርብ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የኀብረቱ 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አዘጋጅ አገር በመሆኗ ብቻ ልዩ ትርጉም የሚሰጣት ሳይሆን ቅኝ ግዢን ከአፍሪካ አህጉር ለማስወገድ ባደረገችው ግንባር ቀደምት ትግል ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤምባሲዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካ ኀብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ፕሮፌሰር መኮንን ገልጸዋል።

እንደ ኢሬቴድ ዘገባ አውሮጳውያን አቆጣጠር 1955 የቀድሞ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ከመሰረቱት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን የድርጅቱ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግላለች። የአፍሪካ ኀብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በመጪው ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ከተከበረ በኋላ ኢትዮጵያ ኀብረቱን በሊቀ መንበርነት ትመራለች።