ኢትዮ-ቴሌኮም የሞባይል ተጠቃሚዎችን 51 ሚሊዮን ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2005 (ዋኢማ) : ኢትዮ - ቴሌኮም ከሞባይል አገልግሎት ጋር ተያይዞ የደንበኞቹን ቁጥር ከሶስት እጥፍ በላይ እያሳደገ መሆኑን ገለጸ።

ከሁለት ዓመታት በፊት 6 ሚሊዮን የነበረው የደንበኞች ቁጥር አሁን 20 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ በቀጣይ ደግሞ ቁጥሩን 51 ሚሊዮን ለማድረስ ነው እየሰራ ያለው።

በሌሎች አገልግሎቶች ላይም እንዲሁ የደንበኛውንም ይሁን የአገልግሎቱን መጠን ለመጨመር ታቅዷል።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በሁሉም አገልግሎቶች ላይ የተጀመሩት 26 ፕሮጀክቶች በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቁ፤ ከአገልግሎቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮች በሙሉ እንደሚቀረፉ ኩባንያው ትናንት ከደንበኞቹ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ አረጋግጧል።

ኩባንያው አሁን ከሚሰጣቸው በተጨማሪ አዳዲስ አገልግሎቶችን የመጀመር ዕቅድ እንዳለው መግለፁን የኤፍቢሲ ዘገባ ያስረዳል።