ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከኳታሩ አሚር ጋር ተወያዩ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2005(ዋኢማ)- ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከኳታሩ አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ከሊፋ አል ታኒ ጋር ተወያዩ።

በመንግስታቱ  ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዶሃ የሚገኙት  ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ትናንት  ከአሚር ሼክ ሃማድ ቢን ከሊፋ አል ታኒ ጋር ባደረጉት  ውይይት የሁለትዮሽ ጉዳዮች ተነስተው ምክክር ተደርጎባቸዋል።

አቶ ሀይለማርያም በአሚር ሼክ ሃማድ ቢን ከሊፋ አል ታኒ  የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ሁለቱ  መሪዎች  ከተወያዩ በኋላም የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ  ማእድን መፈለግና ማውጣትና ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በአገሪቱ መስራት የሚያስችላቸውን  የመግባቢያ ስምምነት አገራቱ መፈራረማቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።