የሴካፋ ዋንጫ በጥሩ ሶስተኝነት ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዛሬ ዕለት ጨዋታውን ያካሂዳል

  • PDF

በ36ኛው የሴካፋ ዋንጫ በጥሩ ሶስተኝነት ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ለግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ይጫወታል፡፡

በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሩብ ፍፃሜ ላይ ደርሷል፡፡

ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረገው ውድድርም ትናንት ህዳር 24/2005 ጀምሯል፡፡

በወጣው መርሀ ግብር መሰረት ህዳር 24/2005 ከሚከናወኑ ሁለት ጨዋታዎች መካከል ኡጋንዳና ኢትዮጵያ ዳግም የሚገናኙበት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ተከታዩ ዙር ያለፈው በምድቡ በኡጋንዳና በኬንያ ተሸንፎ ሱዳንን ብቻ አንድ ለዜሮ አሸንፎ በጥሩ ሶስተኝነት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በምድቡ ሁለት ግዜ ሲያሸንፍ አንዱን 1 ለ 0 የተሸነፈው በአስተናጋጇ ኡጋንዳ ነበር፡፡ በሩብ ፍፃሜ ደግሞ ህዳር 25/2005 አንድ ሰዓት ላይ ለመጫወት ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡ ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ከተሰለፋ ቡድን ተጫዋቾችን ለመመልመል አላማ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሳትፎ ኡጋንዳን ማሸነፍ ከቻለ ጥሩ ስኬት መሆኑን ዋና አሰልጣኙ ስዩም ከበደ ገልፀዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ከኡጋንዳና ኢትዮጵያ በፊት በቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርዴቪድ ሚቾ የምትመራው ሩዋንዳና ታንዛኒያ 10 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ቡሩንዲ ከዛንዚባር፣ ኬንያ ከማላዊ ሲሆን፤ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ ህዳር 25/2005 ይደረጋሉ፡፡

በቀጣይ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ አሸናፊ ከሩዋንዳና ታንዛኒያ አሸናፊ፣ የቡሩንዲና ዛንዚባር አሸናፊ ደግሞ ከኬንያና ማላዊ አሸናፊ እንደሚገናኙ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል፡፡