ጀርመን ለአፍሪካ ህብረት የ30 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረገች

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2005 (ዋኢማ)¬ የጀርመን መንግስት ለአፍሪካ ህብረት የ30 ሚሊዮን ዮሮ ተጨማሪ ድጋፍ አደረገ፡፡

ገንዘቡም ለሰላምና ደህንነት፣ ለአነስተኛ ንግድ፣ ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ግንባታ ድጋፍና ለአቅም ግንባታ የሚውል ነው፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኢራስተስ ምዌንቻ እንዳሉት የጀርመን መንግስት ለህብረቱ የሚያደርገው ድጋፍ ከፍተኛ ነው፡፡

የጀርመን መንግስት ተወካዮች በበኩላቸው የአህጉሪቱን ፀጥታና ደህንነት እንዲሁም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ለመደገፍ ጀርመን ቁርጠኛ አቋም አላት፡፡

እንደ ኢሬቴድ ዘገባ ጀርመን ለአፍሪካ ህብረት ባለፉት አራት አመታት አንድ ነጥብ አራት ቢሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርጋለች፡፡