ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ

  • PDF

አዲስ አበባዕ ህዳር 17/2005 (ዋኢማ) - ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ። በሩጫውም ከ36 ሺ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ አትሌቶችና የበርካታ አገሮች አባሳደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውድድሩ ከአገር ውስጥ ታዋቂ አትሌቶች በተጨማሪ ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ኩጋንዳ ፣ ከጀርመን፣ ከአየርላንድ፣ ከእንግሊዚ፣ከ ጃፓን ሲውዘርላንድ፣ ከእስራኤልና ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ በርካታ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውድድሩም የባንክ ክለብ ተወዳደሪ የሆነችው አበሩ ከበደ ከሴቶች አንደኛ ስትወጣ በወንዶች ደግሞ የትግራዩ ሃጎስ ገብረህይወት ቀደሚ በመሆን እያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር ተሸላሚ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለ170 ሺ ለሚሆኑ ተወዳደሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል።

ውድድሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አቶ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሲሆኑ በውድድሩ ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ጨምሮ ታዋቂ አትሌቶችና ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ከውድድሩ የሚገኘው ገቢ አዳዲስ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ በርካታ የበጎ አድራጎት መህበራትን ለማጠናከር እንደሚውል ተነግሯል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተጀመረ 12 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሲጀመር የነበረው የተሳታፊ ቁጥር 10 ሺህ ብቻ እንደነበርናበአሁን ወቅት የተሳታፊው ቁጥር ከሶሰት እጥፍ በላይ ማደጉ ተገልጿል።