የብአዴን 32ኛ ዓመት በዓል በደብረብርሀን ዩኒቨርሰቲ በድምቀት ተከበረ

  • PDF

አዲስ አበባዕ  ህዳር 17/2005 (ዋኢማ) - የደብረብርሀን ዩኑቨርስቲ ማህበረስብ የብአዴን አባላት ከድህነት ለመዉጣት የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የልማት ራዕይ አዉን ለማድረግ የሚሰሩ መሆናቸዉን አረጋገጡ።

የዩኒቨርሰቲዉ የብአዴን አባላት የ32ኛዉን የብአዴን የልደት በዓል ዛሬ በፓናል ወይይትና በተለያዩ ሥነ ጹሁፍ ዝግጅት ባከበሩበት ወቅት እንደገለጹት ብአዴን ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በትጥቅ ትግሉ ደርግን አሰወግዶ ሰላም፤ ልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት በመገንባት ድህነትን ለማሰወገድ ያደረገዉ ትግል ቀላል አይደለም።

በፖለቲካ ፤በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ ዘርፎችና በመልካም አሰተዳዳር ያካሄደዉ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጉን የፓናሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል ።

ተሳታፊዎቹ በሀገሪቱ የተጀመረዉ የልማት ጥረት ዉጤት አንዲያመጣ በማድረግ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድህነትን ለማጥፋት የጀመሩትን ራዕይ ዕዉን ለማድረግ ዕዉቀታቸዉን ድህነት ተኮር የልማት ሥራ ላይ በማዋል የሚሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የደብረብርሀን ዩኑቨርሰቲ ብአዴን አስተባባሪ አቶ ባዩ ከበደ በበኩላቸዉ ዩኑቨርሰቲዉ የተጣለበትን የተማረ የሰዉ ኃይል ማፍራት በብቃት ለመወጣት የመማር ማስተማር ተገባር በሰላማዊ መንገድ በማሰቀጠል በሁሉም የልማት መሰኮች የተገኙትን ተጠባጭ ለዉጦች ለማሰቀጠል የበኩሉን ደርሻ መወጣት ያለበት መሆኑን አስታዉቀዋል።