የአፍሪካ ስታትስቲክስ ቀን ተከበረ አርብ, 23 ህዳር 2012 16:07

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ህዳር 15/2005 (ዋኢማ) - ስርዓተ ፆታን ያማከለ የስታትስቲክስ መረጃ የሀገራትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ፡፡

የአፍሪካ ስታትስቲክስ ቀን ″ስርዓተ ፆታን ያካተተ ስታስቲካዊ መረጃዎችን በማመንጨት ልማታችንን እናፋጥል” በሚል መርህ በሂልተን ሆቴል ተከብሯል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃም ተከስተ እንዳሉት ጥራት ያለው መረጃን ለህብረተሰቡ ለማድረስ እና ተጠቃሚ የማድረግ ሰራዎች እየተከናወኑ ስርዓተ ፆታዊ መረጃን ማጠናከር ለፖሊሲ አውጪዎች ሴቶችን ለማብቃትና ፆታዊ እኩልነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ማስተር ቢኖይት ካላሳ በዓሉ ለየሀገራቱ ህዝቦች በቂ ግንዛቤ ለመፍጠርና በጋራ እንዲሰሩ አጋዥ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ኢሬቴድ ዘገባ የማዕከላዊ ስታትሲቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ በበኩላቸው ኤጀንሲው ባለፉት 50 ዓመታት በመረጃ አሰጣጥ ሂደቱ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎችና የኤጀንሲው የ50 ዓመት ጉዞ የሚሳይ አውደ ርዕይ ቀርቧል፡፡