ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ፤  ህዳር 10/ 2005 (ዋኢማ) - የእናቶችንና የህጻናትን   ሞት   ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ  የሚያስችል   መርሃ  ግብር  ነድፎ   እየተንቀሳቀሱ መሆኑን  የጤና  ጥበቃ  ሚኒስቴር  ገለጸ ፡፡

በሚኒስቴሩ የብሔራዊ  የእናቶችና የህጻናት  ጤና  አስተባባሪ  ዶ/ር  ቴዎድሮስ  በቀለ ለዋልታ እንደገለጹት የእናቶችንና የህጻናትን  ሞት ለመቀነስ   በቅድመ ወሊድ፣  በድህረ  ወሊድ፣   በጤና  ኤክስቴንሽንና  የቤተሰብ እቅድ  አገልግሎት  መርሃ ግብሮችን  በመጠቀም  የተጠናከረ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ 

በ2003 ዓ/ም  መጨረሻ 15 በመቶ የነበረው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ሽፋን በ2004 ዓ/ም  ወደ 20  በመቶ ማደጉን  የገለጹት   ዶክተሩ በጤና  ኤክስቴንሽን  የሚሰጥ  የወሊድ  አገልገሎትም   35  በመቶ ማደጉን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው  የበጀት አመት  56  በመቶ  የነበረውን  የቤተሰብ  እቅድ አገልግሎት  ተጠቃሚ  እናቶች  ቁጥር   በያዝነው   አመት   76  በመቶ  ለማድረስ  የተለያዩ  እንቅስቃሴዎች  እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡