ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን ማበረታቻ ዛሬ ይቀበላሉ

  • PDF

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 6 /2005 ( ዋኢማ) - ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ዛሬ  በኤድናሞል ህንጻ በሚከናወን ስነ ስርአትይቀበላሉ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ከሆነ የተለያዩ ድርጀቶችና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ከነዚህ መካከልም  አቶተክለብርሀን አምባዬ፥የብሄራዊ ቡድኑ የልምምድ ሜዳበ መገኘት ለእያንዳንዱ ተጫዋች ለመስጠት ቃል የገቡትን፥ የ25 ሺህ ብር ሽልማት ዛሬ ከ5 ሰአት ጀምሮ በኤድናሞል በሚከናወነው ስነ ስርአት ያበረክታሉ።

ከገንዘብ ሽልማቱበ ተጨማሪ፥ለቡድኑ አባላት በሙሉ የምሳ ግብዣ እንደሚደረግላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

ድሉን ተከትሎ የሚድሮ ክባለቤት ሼክሙሀመድ አሊ አላሙዲ ለብሄራዊ ቡድኑ በአጠቃላይ የአምስት ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ  ቃል መግባታቸው ይታወሳል።