ለ15ኛው ዓለም አቀፍ የታዳጊ አገራት የከተማ ህዝብ እንቅስቃሴ ትብብር ጉባኤ ዝግጅት እየተደረገ ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 /2005 (ዋኢማ) - በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 15ኛው አለም አቀፍ የታዳጊ አገራት የከተማ ህዝብ እንቅስቃሴ ትብብር ጉባኤ የተሳካ ለማድረግግጅት እየተደረገ መሆኑን አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ።


የኮሚቴው አስተባባሪ አቶ በድሉ አሰፋ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት የአዲስ አበባ አስተዳደር ኮዳቱ ኢንተርናሽናል ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበርጉባኤው ስኬት የሚረዱ ዝግጅቶች እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ጉባኤው
ከጥቅምት 12-15/2005 ዓ/ም በአፍሪካ ህብረት የመሰብሳቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድም አስተባባሪው ተናግረዋል።


በጉባኤው ከ700 በላይ የአገር ውሰጥና የውጪ አገራት ታዳሚዎች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ በድሉ ጉባኤው መልማት ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ የህዝብ ዝውውርን የተመቻቸ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።


በጉባኤው ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሁም የተለያዩ የፖሊሲ ሀሳቦችና አቅጣጫዎች ስለሚቀረቡ በሃገራት መካከል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚያግዝም  አስተባባሪው ተናግረዋል።

የተለያዩ አገራት የትራንስፖርትና የከተማ ልማት ሚኒስትሮችና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያ ሃላፊዎችም በጉባኤው ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡







 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results