ሶማሊያዊያን ሀገራቸውን መልሶ በመገንባት ተሳትፏቸውን ማጠናከር አለባቸው -የአፍሪካ ህብረት

  • PDF

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2005 (ዋኢማ ) - ሶማሊያውያን መሪያቸውን ሲመርጡ ያሳዩትን ሰላም ወዳድነትና ቁርጠኝነት ሀገራቸውን መልሶ በመገንባቱ ስራ ላይም ሊደግሙት እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዣን ፒንግ አሳሰቡ፡፡

አዲስ በተመረጡት በሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ማሀሙድ በዓለ ሹመት ላይ የተገኙት ሊቀመንበሩ ዣን ፒንግ እንዳሉት ሶማሊያና ህዝቦ ለዚህ ታሪካዊ እለት እንዲበቁ ድጋፍ ያደረጉ የህብረቱ አገሮችን አመስግነዋል፡፡ ኮሚሽኑ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንደመለከተው ሊቀመንበሩ በሶማሊያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የሶማሊያውያኑና የወቅቱ የሽግግር መንግስት ሚና ግንባር ነበር ብለዋል፡፡

ይህ ተሳትፎቸውም በቀጣይ በሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲን እንዲሁም ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረትም በሀገሪቱ የሚደረገውን የልማትና የሰላም እንቅስቃሴ በማንኛውም መልኩ እንደሚደግም ተናግረዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ በመቆድሾ ከተማ ከትናንት በስትያ በተካሄደው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ማሀሙድ በዓለ ሹመት ላይም የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መገኘታቸው ይታወሳል፡፡


  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 171 guests