ከኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

  • PDF

 

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤትመስከረም 4 ቀን የጀመረውን ሰብሰባ በዛሬው እለት በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በዚህ ስብሰባው ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ተግባራዊልዕልናን በማረጋገጥ የመለስ/ኢህአዴግን ራዕይ እናሳካ›› በሚል ሰነድ ላይእንዲሁም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ፣ ተሞክሮዎቻችንና አለም አቀፍልምዶችን በመቀመር ‹‹የአመራር ግንባታና የህዳሴው ጉዞ›› በሚል ርዕስቀደም ሲል በታላቁ መሪ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ እንዲሁም በእስካሁኑየእድገትና ትራንስፎርሜሽን አቅድ አፈፃፀምና በ2005 የመንግስትና የድርጅትተግባራት እቅድ ላይ ተወያይቷል፡፡

በምክር ቤታችን ስብሰባ የታላቁን መሪ የጓድ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎየሀገራችን ህዝቦች፣ አፍሪካውያን ወገኖቻችን እንዲሁም የታላላቅ አህጉራዊናአለምአቀፋዊ ድርጅቶችና መንግስታት መሪዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንበመግለፅና ለሀገራችን በጎ በመመኘት ያደረጉትን እንቅስቃሴ በማድነቅየታላቁ መሪያችንንና የድርጅታችንን የለውጥ ራዕይ ቀጣይነት ለማረጋገጥበድርጅት፣ በመንግስትና በህዝብ አደረጃጀት አማካኝነት መረባረብ እንደሚገባአፅንኦት ሰጥተን ተወያይተናል፡፡

የአመራር ግንባታና የህዳሴው ጉዞ በሚል ርዕስ በጓድ መለስ ዜናዊ ተዘጋጅቶከሁለት ወራት በፊት በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በፀደቀው ሰነድ ላይባደረግነው ውይይት የህዳሴ ጉዟችንን ለማጠናከር በድርጅት ውስጥከአባላትግንባታ አንስቶ እስከ ስልጠናና አመራር ግንባታ ድረስ በየደረጃውየሚከናወኑ ተግባራት ላይ እንዲሁም የመንግስታዊመዋቅራችንን ብቃትለማጎልበትና የአፈፃፀም ሂደቱን ለማጠናከር መከናወን ያለባቸውን የአቅምግንባታ ስራዎችንከዚህም ጋር በተያያዘ የህዝቡ የተለያዩ አደረጃጀቶችጎልብተው የሚወጡበትንና የልማት ጉዟችንን የሚያደናቅፉየኪራይ ሰብሳቢነትአመለካከትና ተግባራትን ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍ የምንታገልበትንናየህዝቡን ተጠቃሚነትለማረጋገጥ የምንችልበትን ሁኔታ በዝርዝርተመልክተናል፡፡


ምክር ቤታችን ይኸው ሰነድ የኢህአዴግ ሰነድ ሆኖ በየደረጃው ውይይትእንዲካሄድበትና ከዚህም አልፎ በሰነዱ ውስጥየተመለከቱትን ተግባራትበአፋጣኝ ወደ ተግባር
ማሸጋገር እንደሚኖርባቸው በውሳኔው አረጋግጧል፡፡


ምክር ቤታችን በእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም አጭር ግምገማናበ2005 የትኩረት አቅጣጫ ሰነድ ላይምተወያይቷል፡፡ በዚሁ ውይይት ያለፉትንሁለት ዓመታት የእቅዱን አፈፃፀም ተመልክቶ የነበሩትን ልምዶችመነሻበማድረግ እቅዱን በላቀ ደረጃ ለማስፈፀም በከፍተኛ ቁርጠኝነትለመንቀሳቀስ ወስኗል፡፡

ምክር ቤታችን ከታላቁ መሪ ዕረፍት በኋላ የተፈጠረውን ሰፊ ህዝባዊእንቅስቃሴ እንደበጎ አጋጣሚ በመውሰድ ሁሉምሴክተሮች የተቀመጠውንየእድገትና ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ ግብ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባቸውአመልክቷል፡፡

የመንግስትን የገቢ አቅም የማጠናከር ስራን በተመለከተ ዘንድሮ ከአምናውበ50 በመቶ ለማሳደግ እንዲሁም ቁጠባንበማጠናከር ኢንቨስትመንትለማጎልበትና በእቅዱ ውስጥ የተያዙትን አበይት ፕሮጀክቶች ለማሳካትመረባረብእንደሚገባ ምክር ቤታችን አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይቷል፡፡ በተለይምየኤክስፖርት ምርታችንን የማሳደግና የውጭምንዛሬያችንን በቁጠባ በመጠቀምእቅዶቻችንን የማሳካት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንን በማስፋፋትከውጪየሚገቡ ምርቶችን የመተካት ስራ ማከናወን እንዳለብን ምክር ቤታችንአስምሮበታል፡፡


የኢህአዴግ ምክር ቤት በህዝቡ ኑሮ ላይ ጫና ያሳረፈውን የዋጋ ግሽበትለመቆጣጣር እስካሁን የተደረገውን ውጤታማእንቅስቃሴ የገመገመ ሲሆንአሁንም የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠርና ለመመከት በገጠርም በከተማ የህዝቡንገቢበማሳደግ እንዲሁም ምርታማነትን በማሳደግና በሌሎች የፖሊሲመሳሪያዎች በመታገዝ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባበዚህም በዓመቱ አጋማሽላይ የዋጋ ግሽበቱን ትርጉም ባለው ደረጃ ለማውረድ እንደሚቻል አመልክቷል፡፡


በስብሰባችን የቀጣዩን ዓመት የድርጅትና የመንግስት ስራዎች የአፈፃፀምአቅጣጫ በዝርዝር የተመለክትን ሲሆንእቅዶቻችንን ለማሳካት በገጠርምበከተማም የተጀመረውን የለውጥ አቅም ግንባታ አጠናክረን መቀጠልእንደሚገባን፤በመሆኑም በድርጅት፣ በመንግስትና በህዝብ አደረጃጀቶች ደረጃየሚከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ማቀድና መፈፀም፤ በጎልምዶችን መቀመርናማስፋፋት እንደሚገባም ተመልክተናል፡፡


በተጨማሪም ሀገራችን በጓድ መለስ አመራር በአካባቢያችንም ሆነ በአህጉራችንስትጫወተው የነበረውን በጎ ሚና እናመልካም ተቀባይነት አጎልብታ መቀጠልእንዳለባት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ልታበረክት የምትችለውንበጎአስተዋፅኦ እንድታበረክት የኢህአዴግ አመራር ሚናውን እንደሚጫወትአረጋግጠናል፡፡

በመጨረሻም በጓድ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት የተፈጠረውን የአመራርክፍተት ለመሙላት ባካሄድነው ምርጫ ጓድኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግሊቀመንበር እንዲሁም ጓድ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርሆነውእንዲያገለግሉ በመሰየም የሁለት ቀናት ስብሰባችንን በተሳካ ሁኔታናበከፍተኛ የመነሳሳት ስሜት አጠናቀናል፡፡

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች!

የሰጣችሁንን ታላቅ አደራ በፅናት በመሸከም የታላቁ መሪያችንንናየድርጅታችንን ራዕይ ለማሳካት ቀን ከሌትእንደምንረባረብ በዚህ ታሪካዊ ቀንድርጅታችን ቃሉን ያድሳል፡፡ ሀገራችንን ከድህነት በማውጣት በብልፅግናጎዳናእንድትራመድ ለማስቻል፣ እናንተም የበለፀገ ኑሮ እንድትገፉ ለማድረግ፣ከመላ የአካባቢያችንና የአህጉራችን ህዝቦችጋር በጋራ ጥቅምና በመከባበር ላይየተመሰረተ ግንኙነታችንን አጠናከረን ለመቀጠል በምናካሂደው ትግልእንደከዚህበፊቱ ሁሉ የተሟላ ተሳትፏችሁ እና ድጋፋችሁ እንደማይለየንእንተማመናለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ኢህአዴግና መላአባላቱ በድርጅታችን እናበእናንተው ጥረት የተጀመረው የኢትዮጵያ ህዳሴ ጉዞ ዳር እንዲደርስከመቼውም በላቀየትግል ወኔ ለመረባረብ ቃላችንን እናድሳለን፡፡

የተከበራችሁ የድርጅታችን አባላት!


በድርጅታችን ሊቀመንበር በታላቁ መሪያችን በጓድ መለስ ህልፈት ከደረሰብንከፍተኛ ሀዘን ወጥተን እሱ ያሰነቀንንራዕይ አንግበን ከመቼውም ግዜ በላቀሁኔታ ወደፊት ለመራመድ የሚያስችለንን ሰፊ መነቃቃትና አቅጣጫጨብጠንስብሰባችንን በድል አጠቃለናል፡፡

መላ የድርጅታችን አባላት እስካሁን በከፍተኛ ትጋትና ቁርጠኝነት ስታደርጉትእንደነበረው ሁሉ የተሰጣችሁን ተልዕኮበማሳካት የታላቁ መሪያችንንየመለስንና የድርጅታችንን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ከመቼውም ግዜ በላቀ ወኔእራሳችሁንከጥገኛ አስተሳሰብና ተግባር በማጥራት እንዲሁም የተፈጠረውን ሰፊህዝባዊ ማዕበል ወደ ላቀ ስኬት በመምራትበቁርጠኝነት እንድትረባረቡጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን፡፡

የተከበራችሁ የትግላችን አጋሮችና ደጋፊዎች!


በስኬት የተጠቃለለው የምክር ቤታችን ስብሰባ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎችአንግበን ከእናንተ ጋር እንደተለመደውበጋራ ለመስራት ያለንን ቃል ያደስንመሆናችንን ስናረጋግጥላችሁ እናንተም እንደወትሮው ሁሉ ከጎናችንተሰልፋችሁለመረባረብ ዝግጁ መሆናችሁን በመተማመን ነው፡፡


ምክር ቤታችን በዚህ አጋጣሚ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ለምትገኙየትግላችን ደጋፊዎች በሙሉ የታላቁ መሪያችንንአደራ አንግበን ለጋራጥቅምና ደህንነታችን ለምናደርገው ተልዕኮ የተለመደ ድጋፋችሁንእንድትሰጡን ጥሪውንያቀርብላችኋል፡፡

የተከበራችሁ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመታገል የምትንቀሳቀሱተቃዋሚ ፓርቲዎች!

በታላቁ መሪያችን ድንገተኛ ህልፈት የደረሰብንን ሃዘን ለመካፈል የሃዘንመግለጫ በማውጣትና በአካልም በመገኘትስላፅናናችሁን ከፍተኛ ምስጋናችንንእናቀርብላችኋለን፡፡ የኢህአዴግ ምክር ቤት የሀገራችን የመድብለ ፓርቲስርዓትተጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬም በፅናት ለመንቀሳቀስ ያለውን ቁርጠኝነትእየገለፀ ዘንድሮ የሚካሄደውን የአዲስ አበባናአካባቢ ምርጫ ነፃ፣ ግልፅናፍትሃዊ ለማድረግ በጋራ ምክር ቤታችን አማካኝነት በሚያስማሙን ጉዳዮችላይበመተባበር በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ደግሞ በሰለጠነ መንገድ በመታገልበትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናችንንእንገልፅላችኋለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሀገራችን ህዳሴ ለማረጋገጥ በተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴእጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንሰራ በድጋሚጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን፡፡