አለህ ተተኪ በላደራ

  • PDF


በነሐሴ እኩሌታ ላይ በማክሰኞ ዕለት ማለዳ
የተዘጉ አንደበቶችን ሁሉ በድንጋጤ ያፈነዳ
በየቤቱ ሀዘን ገባ ቅስም ሰባሪ ያልተለመደ ነገር እንግዳ
ሞገድ እንዳናወጠው ባህር በማዕበል እንደተመታ
ሀገር ሁሉ ተመመ ተጓዘ በቀን በማታ
ከደጃፍህ ደርሶ የቁጭት/የስስት/ እንባውን ሊረጭ
መለስ ቀና ብለህ ብታይ ትመለከት ነበረ የሰው ነጭ
ይሄ ሁሉ የሰው መውደድ ይሄ ሁሉ የፍቅር ለዛ
በየትኛው የዘይቤ ዓይነት ይገለጻል እንደዋዛ
ድሆችህ ከደጅ ሲንጫጩ ሲረግፉ እንደጤዛ
ድህነት ጠሉ አባታችን ጠፋ ተስፋችን  ሁሉ ጨለመብን
ከረሃብ አለንጋ የታደገን ሰርቶ መብላት ያሳየንን
ምነዋ በዋዜማው በአዲሱ ዓመት መዳረሻ
ጀምሩን ሳይቋጭ  ሄደ ተነጠቀብን በሞት ዋሻ
ወጣቱም ውለታ አለብኝ ከትቢያ ላይ አንስቶ ቀና አርጎኛል ከጎዳና
ድንጋዩን ዳቦ አድርጎ ረሃቤን አስታግሷልና
ሴቷም በበኩሏ ዛሬ ከጓዳ አውጥቶኛል አደባባይ ውያለሁ
ምስጋና ይግባው እና ለነጻነት በቅቻለሁ
አሁን ቀና ብዬ እንድሄድ ድፍረት እንደበት አግኝቻለሁ
አለች አናቶችም በሀዘን ዋይታ ደረታቸውን በመደለቅ
ለኛ ህንጻ ቤት ሰርቶ አሳርፎን እሱ ግን ዕረፍት ሳያቅ
ባልጠበቅነው መንገድ አየን ጀግናው ሲወድቅ
እያሉ አረገዱ ምድር በጫጩት ታሰሰ
መላው ሀገሩ ጨለመ የሀዘን ድባብ ለበሰ
ዕድሜ ጾታ ዘር ሳይለየው ሁሉም ተንከባለለ
ወጣት ሕጻኑ ጎልማሳ አዛውንቱ ሁሉ ዋለለ
አጥቢያው ኮኮቡ ነጸብራቅ ዕንቁ ባለራዕይ ሳታና
ተፈጥረህ ነበር ተከስተህ ኢትዮጵያዊው ባለዝና

አዲስ ተልዕኮ ሰንቀህ የሥራ ባህልን የቀየርክ
የሀገር ዕድገት ናፋቂ የሕዝቦች ኩራት  እኮ ነበርክ
ግና የጀግና ልጅ ጀግና ነው እየበገሬ መራራ፣
ከጥንካሬህ የወረሰ የታተመ ባንተ አሻራ፣
አለ የነገን ተስፋ ያነገበ አለህ ተተኪ ባላደራ፣
ባንተ ብሩህ አእምሮ ውስጥ  የታለመው ያ ታላቅ ግብ
በወጣቱ ክንድ ውጤቱ አምሮ ለትውልድ ሁሉ እንዲያብብ
የክፍለ ዘመኑን ታላቅ አደራ ቃል ኪዳኑ ሊያስጠብቅ
ሆ ብሎ በአንድ ቃል ተሟል ጅምር ውጥንህን ሊያጠናቅቅ
በእንባው መሐላ ገብቷል ለቃልህ ሊሰዋ ከሊቅ እስከ ደቂቅ



መታሰቢያነቱ
ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ



ከፍቅርተ ገ/አምላክ
ነሐሴ/2004
አዲስ አበባ

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 481 guests