እሳትና የዓለም ምድራዊ አቀማመጥ

  • PDF

እሳት የዓለምን ምድራዊ አቀማመጥ ቅርጽ በማስተካከል ረገድ ወሳኝ ሚና አለው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት ተፈጥሯዊ በሆነ ሰደድ እሳት ምክንያት ባለ አበባ ተክሎች እንዲስፋፉ ምክንያት እንደሆኑ የሚጠቁም መረጃ መገኘቱን የጠቆመው ዘገባው፤ በከፍተኛ ሙቀት ወይም በከፍተኛ የኦክስጂን መጠን መጨመር የእሳቱ መነሻ እንደ ነበርም አስቀምጧል፡፡ እሳቱ በተለይ አነስተኛ ባለአበባ ተክሎች ለማበብ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆንላቸው ተገልጿል፡፡                                                                                                        

በሮያል ሆልዌይ ዩኒቨርስቲ የመሬት ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት አንድሪው ስኮት እንዳሉት ያ ወቅት ባለ አበባ ተክሎች ለመፈጠራቸውና ለመስፋፋታቸው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ ስለ እሳቱ መፈጠርም በምክንያትነት በዛን ወቅት ነበረው የኦክስጂን መጠን ከፍተኛ መሆኑ ሲሆን በወቅቱም የነበረው መጠን 25 ከመቶ ያህል እንደ ነበር ግምታቸውን አስቀመጠዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን 21 በመቶ ብቻ ነው፡፡
/አዲስ ወሬ/