22 May 2013
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሀሙስ ይፈፀማል
አዲስ አበባ ነሀሴ 14/ 2004/ ዋኢማ/ - የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሀሙስ ነሀሴ 17 እንዲፈፀም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲነዶስ ወሰነ።
ቅዱስ ሲኖዶሱ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ቀብራቸው አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንዲካሄድ ነው የወሰነው።
በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይም የተለያዩ አገራት የሀይማኖት መሪዎች እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል።
እስከ ቀብራቸው ድረስም የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ አቡነ ፊሊጶስ ስራዎችን እንዲመሩ ሲኖዶሱ ወስኗል።
| < Prev | Next > |
|---|


