25 May 2013
በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ 7ሺ300 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ተከፋፈሉ
አዲስ አበባ ነሀሴ 14/ 2004/ዋኢማ/- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ መልሶ ማልማት እና በሌሎች ነባር ሳይቶች የገነባቸውን 7ሺ 300 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ትናንት ከሰዓት በዕጣ አከፋፈለ፡፡
ቤቶቹ የተገቡት በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ቂርቆስና የካ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ነው።
ለ7ኛ ዙር በወጣው ዕጣ ሴቶች 30 በመቶ ቅድሚያ ወስደዋል፡፡
ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አገር አቀፍ ፕሮጀክት ከተጀመረ ወዲህ ከ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጅነር ኃይለመስቀል ተፈራ ተናግረዋል።
በሕዝብ ፊት የተደረገውን የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ያስጀመሩት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በበኩላቸው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ የመጠለያ ችግሩ ይፈታል፤ የከተማዋ ገጽታም ይለወጣል ብለዋል፡፡
ትናንት ዕጣ የደረሳቸውን ጨምሮ በልማት የተነሱ 15ሺ ሰዎች በዚህ ዓመት የኮንዶሚኒየም ቤት ወስደዋል፡፡ ሌሎች 84 ሺ ቤቶች ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው ብለዋል።
| < Prev | Next > |
|---|


