ህብረቱ በሶማሊያ የሰላም አስካባሪ ኃይል በሞቃዲሾ የሚካሄደውን ግድያ አወገዘ

  • PDF

አዲስ አበባ ነሃሴ 9 /2004 /ዋኢማ/ - በሶማሊያ የአፍሪካ ኀብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል /አሚሶም/ በሞቅዲሾ የሚያካሂደውን ግድያ አወገዘ። የሶማሊያ ባለስልጣናት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱም ጠይቋል።


በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ልዩ ተወካይ አምባሳደር ቦዩባካር ዲአራ እንዳሉት በሞቅዲሾ የሚያካሂደውን ግድያ የሶማሊያ ባለስልጣናት ሊያስቆሙ ይገባል።


በዋና ከተማዋ የሚካሄዱ የነበሩ የመብት ጥሰቶች ካለፈው ዓመት ጀምሮ የቀነሰ ቢሆንም ጋዜጠኞችን፣ የመንግስት ባለስልጣናትንና ነጋዴዎችን ነጥሎ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል።


የሶማሊያ ባለስልጣናት ተቋማዊ ምርመራ በማድረግ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱትን ለሕግ እንዲያቀርቧቸው አምባሳደር ቦዩባካር ዲአራ አሳስበዋል።


ባለስልጣናቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱትን ሰዎች ለፍርድ ለማቅረብ በሚያደርጉት ጥረት በሶማሊያ የአፍሪካ ኀብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል /አሚሶም/ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።




  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 203 guests