በመንግስት ሆስፒታሎች ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ የህክምና መሳሪያዎች ሊወገዱ ነው

  • PDF

በአገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋሉና በተደጋገሚ ብልሽት የሚደርስባቸው የህክምና መሳሪያዎች ሊወገዱ ነው።

ኢትዮጵያን ባዮ-ሚዲካል ላብራቶሪ ኢኩዊፕመንት ኢንጀንሪንግ ማህበር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በተደጋገሚ ብልሽት የሚደርስባቸውን መሳሪያዎችን የማስወገድ ስራ መጀመሩን ነው የገለፀው።

ለማስወገድ ስራው ባዮ-ሚዲካል ላብራቶሪ ቴክኒሽያኖች ቡድን በትላልቅ የመንግስት ሆስፒታሎች ለማቋቋም ጥረት እየተደረገም ይገኛል ብሏል።

በአሁኑ ወቅት በአብዛኞቹ የመንግስት ሆስፒታሎች ከሀያ ዓመት በላይ ያገለገሉና ያረጁ መሳሪያዎች እንደሚገኙና በነዚህ የህክምና መሳሪያዎች ስህተት የሰው ሀይወት እንደሚያልፍ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።