በቻይና ቁልፍ የኢንተርኔት መፈለጊያ ኩባንያ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

  • PDF

በቻይና ቁልፍ የኢንተርኔት መፈለጊያ ኩባንያ የሆነው ባይዱ ኩባንያ ሰራተኞች  ከሌሎች አካላት ገንዘብ ተቀብለው ከድረ-ገጽ ላይ መረጃን በማጥፋት ወንጀል  ተጠርጥረው  መታሰራቸው  ተገለጸ።

ግዙፉ የድረ-ገፅ መፈለጊያ ኩባንያ እስከ አሁን  ሶስት ሰራተኞችን ከሥራ ያባረረ ሲሆን አንዱ ግን በቁጥጥር ሥር አልዋለም፡፡

የባይዱ ኩባንያ ቃል አቀባይ ቤቲ ቲያን እንደገለጹት፤ የሙስና ቅሌቱ የተካሄደው በአስር ሺዎች ዩዋን በሚቆጠር ገንዘብ ተጠርጥረው ነው። የትኛው መረጃ እንዲጠፋ እንደተደረገ የታወቀ ነገር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡    

ሚስቲያን በበኩላቸው ለቢቢሲ በኢሜይል እንደገለጹት፤ የባይዱ ኩባንያ በተደጋጋሚ  ህገ-ወጥ የመረጃ ማጥፋት ድርጊት እንደሚፈጸምበትና ይህን ድርጊት ለመከላከል ጉዳዩን የሕዝብ ደህንነት አካላት እንዲከታተሉት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡  

በተጨማሪም ኩባንያው መረጃ የጥፋት ሥልጣን ለተሰጣቸው ሰራተኞች ተከታታይ  የሆነ የሙያ ስነ-ምግባር ትምህርት እየሰጠ አንደሚገኝ አያይዘው  ገልጸዋል፡፡  
.
ምዕራብያውያን እንደሚናገሩት የባይዱ ኩባንያም ሆነ ሌሎች በቻይና ውስጥ የሚሰሩ የቻይናና የውጪ ድረ-ገጾች የሃገሪቱን ጥብቅ የሆነውን የኢንተርኔት አጠቃቀም  ደንቦች የማክበር ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ 

ግሬት ፋየር ዎል በሚል ሲስተም ቻይና ብዙ ቁጥር ያላቸውን የውጭ ሃገራት ድረ-  ገጾችን እንዳገደች የሚነገርላት ኮምኒስት ሃገር ጥብቅ የሆኑ ደንቦችን በማውጣት ተግባራዊ አድርጋለች  የሚል አቤቱታ ይቀርብባታል፡፡
.
ሆኖም በቻይና በህገ-ወጥ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ኤጄንሲዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በተለያዩ  ኩባንያዎች በኢንተርኔት የሚለቀቁትን ደረጃዎችን ያጠፋሉ፡፡