የጋና ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

  • PDF

አዲስ አበባ ነሀሴ 2/2004/ዋኢማ/ - የጋና ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩት ክዌሲ ቤኮዪ አሚሳህ አርቱር የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ መኃላ ፈጸሙ።

አሚሳህ አርቱር በቅርቡ የጋና ፕሬዚዳንት ሆነው በተሾሙት ጆን ድራማኒ ማህማ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት በዕጩነት የቀረቡ ሲሆን፤ ሹመታቸው ከአገሪቱ ፓርላማ ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል።

በጋና የአመራር ለውጥ ሊከሰት የቻለው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ኢቫንስ አታ ሚሊስ ባለፈው ወር በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።

ተሿሚው ምክትል ፕሬዚዳንት አ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ የጋና ማዕከላዊ ባንክ ገዢ በመሆን የአገሪቱን የግሽበት መጠን ወደ አንድ አኃዝ ዝቅ ማድረግ ችለው እንደነበር ዥንዋን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ኢዜአ ነው።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results