የኦሞ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ነው

  • PDF

ደቡብ ኦሞ ሐምሌ 28/2004/ዋኢማ/- በደቡብ ኦሞ ዞን እየተካሄደ ያለው "የኦሞ ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮጀክት" የአካባቢው ህብረተሰብን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ እየተካሄደ ያለው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በዋነኛነት በአካባቢው ያለውን የአርብቶ አደር ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታን እየቀየረ ይገኛል።

የአካባቢው ህብረተሰብ በ175 ሺ ሄክታር መሬት ላይ እየኖሩ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ደግሞ በግምት 120 ሺ ሄክታር የሚገመት መሬት እንደሚሸፍን የገለፁት አቶ ሞሎካ በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ የቦዲ፣ ሙሪሲና የባቻ በመባል የሚታወቁት የአካባቢው ብሔረሰቦችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

"የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ እየተሰራ ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ብሔረሰቦች የኋላ ታሪካቸው እንደሚያስረዳው ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ አገልግሎቶችን በማግኘት በኩል አነስተኛ እንደነበር ጠቁመው፤ ፕሮጀክቱ መሰራቱ ግን በአካባቢው የሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብን የኑሮ ሁኔታ በመቀየር የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።" ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

እንዲሁም የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በዞኑ መሰራቱ በዞኑ ብሎም በመላው ሀገሪቱ ላለው የህብረተሰብ ክፍል ከፍተኛ የሆነ የስራ እድል እንደሚፈጥር ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
የስኳር ልማት ፕሮጀክቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከፌዴራል፣ ዞንና ከክልል የተውጣጡ ኮሚቴዎች በጋራ ይቆጣጠሩታል።

የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር አርብቶ አደሮች የማስፈሩን ስራ እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ 1ሺ 430 የአርብቶ አደር ቤተሰቦችን የቡርሲ፣ ቦዲና የባቻ ብሔረሰብን ማስፈር መቻሉን ተናግረዋል።

"ከሰፋሪዎች መካከል 606 ቤተሰቦች የእርሻ ቦታዎቻቸውን ሲረከቡ፣ 300 የሚሆኑት ደግሞ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ገንብተዋል፤ ቀሪዎቹ 50 ቤተሰቦች በአዲሱ የሰፈራ መንደር ኖሮዋቸውን ጀምረዋል።" በማለት የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 1 ሺ 742 ቤተሶቦችን በሳላ ማጎ ወረዳ ለማስፈር ያቀደ ሲሆን፤ የሰፈራ ፕሮግራሙን በተያዘው የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዷል ብለዋል።

አቶ ዳርጌ የሁለት ልጆች አባት ሲሆኑ፤ በዘንድሮ አመት የሰፈራ ፕሮግራም በመካተታቸው ከአራት ወራት በፊት በመንደር ቁጥር ሁለት ውስጥ መስፈራቸውን ከመገለጻቸውም በላይ በተለያዩ ጊዜያት ከመንግሥት አመራሮች ጋር ስለሰፈራ ፕሮግራሙ ምክክርና ውይይት ማደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት በፈቃደኝነት በዚህ ቦታ ላይ እንድንሰፍር በማድረጉ የሰፈራ ፕሮግራሙን እንደሚደግፉ የገለጹት አቶ ዳርጌ ከዚህ ቀደም ቤተሰባቸው የመጠጥ ውሃን የሚያገኘው ከኦሞ ወንዝ መሆኑንና ሴቶች የድንጋይ ወፈጮ ለማግኘት ከሁለት እስከ ሶሰት ቀናትን እንደሚጓዙ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሰፈሩበት አካባቢ የድንጋይ ወፍጮ አገልግሎት፣ የንጹህ ውሃ መጠጥና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመግንባት ላይ እንደሚገኙም አቶ ዳርጌ አያይዘው ገለጸዋል፡፡

መንግሥት በስኳር ልማት ፕሮጀክት ምክንያት የአካባቢውን ነዋሪ ከፍላጎት ውጪ አፈናቅሏል መባሉን በጽኑ እንደሚቃወሙ የሚገልጹት አቶ ሞሎካ የመንግሥት መርህ ማሳመን እንጂ ማስገደድ እንዳልሆነ ከመናገራቸውም በላይ ለሁለት አመት ያህል ህብረተሰቡን በሰፈራ ፕሮግራሙ ማወያየታቸውንና አንድም ቤተሰብ ተገዶ ባለመፈናቀሉ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሰፈራ ፕሮግራሙ 1ሺ 746 ሄክታር መሬት ያህል ምንጣሮ እንደተካሄደና በሳላ ማጎ ለሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ለግብርና እንዲውል ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው፤ እያንዳንዱ ሰፋሪ ቤተሰብም አንድ ሄክታር የግብርና መሬት እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዞኑ የአስተዳደር ኃላፊ በበኩላቸው፤ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሰማሩ በማድረግ የአርብቶ አደር ማህበረሰቡ በአካባቢው የሚያካሂደውን ግብርና ለመደገፍ ታቅዷል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም መንግሥት አርብቶ አደሩ በልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የረጅም ጊዜ እቅዱ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው አርብቶ አደሩ የሸንኮራ አገዳን ለማልማት ለኦሞ ኩራዝ የስኳር ፋብሪካ እንዲያቀርብ ይደረጋል ብለ

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 428 guests