በእንግሊዝ የጽሑፍ መልዕክት ንግግርን እየተካ እንደሚገኝ አንድ ጥናት ጠቆመ

  • PDF

ኦፍ ኮም የተባለ ኩባንያ ይፋ ያደረገው አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው እንግሊዛውያን   ብዙውን ጊዜ በሞባይላቸው የስልክ ጥሪ ከማድረግ ይልቅ የጹሑፍ መልዕክት ማስተላለፍ ይቀናቸዋል።

በአጠቃላይ እ.ኤ.አ በ2011 የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት 58 በመቶ የሚሆኑት በዕየለቱ በሞባይል መልዕክት ግንኙነት የሚያደርጉ ሲሆን፤ 47 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የስልክ ጥሪ የሚደረግ እንደሚያደርጉ አመታዊ የደንበኞች ግንኙነት ያወጣው ሪፖርት ያሳያል ፡፡

በአሁኑ ወቅት አንድ እንግሊዛዊ በአማካኝ 50 ያህል መልዕክቶችን በሳምንት ሲያደርግ በመደበኛም ሆነ በሞባይል ስልክ ከሚደረጉት የስልክ ጥሪዎች በቁጥር የሚልቅ ነው ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ለመጀመሪያ ጊዜ በሞባይል ስልክ የሚደረገው የጥሪ መጠን በ1 በመቶ መቀነሱ የታየ ሲሆን፤ በመደበኛ ስልክ የሚደረገው የጥሪ መጠን ደግሞ በ10 በመቶ መቀነሱንና በአጠቃላይ የስልክ ንግግር የሚፈጀው ጊዜ በ5 በመቶ እንደቀነሰ መምጣቱን መረጃ ያሳያል፡፡

የኦፍ ኮም  ኩባንያ የምርምር ዳይሬክተር ጄምስ ቲኬት እንደሚናገሩት ሰዎች ፊት ለፊት ንግግር ማድረግና በስልክ ጥሪ መነጋገርን እንደ ዋነኛ የግንኙነት ዘዴ  መጠቀምን  የሚያቆሙበት ጊዜ ደርሷል ብለዋል፡፡  

ይህም የሚያሳየው  ከጊዜ  ወደ ጊዜ በሞባይል አማካኝነት  የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች  መበራከታቸውን ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት 39 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች የስማርት ሞባይል ተጠቃሚዎች እንደሆኑና ከእነዚህ  ውስጥ   42  የሚሆኑት  የስማርት ሞባይል   አስፈላጊ የሆነ የኢንተርኔት አገልገሎት እንደሚሰጣቸውና 51 በመቶ የሚሆኑት  ደግሞ ኢሜይል ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት  ገልጸዋል ፡፡

በሪፖርቱ እንደተቀመጠው 96 በመቶ የሚሆኑት ከ16 እስከ 24 የእድሜ ክልል  የሚገኙ ወጣቶች በዕየለቱ ከጓደኞቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሞባይል የጹሑፍ  መልዕክት በመላክ እንደሚገናኙ መረጃው የጠቆመ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 90 በመቶ ዋነኛ የጽሑፍ መልዕክት ተጠቃሚዎች እነደሆኑና 73 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ  የማህበራዊ  ደረ-ገፅ  ደንበኛ እንደሆኑ መረጃው ይፋ  አድርጓል፡፡

በተጨማሪ የጥናቱ ሪፖርት እንደሚያትተው ስማርት ሞባይሎች የሰዎችን  የመገበያየት ባህል ከመቀየራቸውም በላይ ደንበኞች ምርቶችን ፍቶግራፍ  እንዲያነሱ፣  ዋጋ እንዲያወዳድሩና የምርቶችን መረጃ መሰበሰብ የሚያስችል አገልግሎት  ይሰጣል፡፡