19 June 2013
በከተማው 76 ሺ 2 መቶ 42 ቶን የግብርና ምርት መገኘቱ ተገለጸ
አዲስ አባበ፤ ሐምሌ 12/2004 (ዋኢማ) - በአዲስ አበባ ከተማ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 76 ሺ 2 መቶ 42 ቶን የእንስሳት፤ የፍራፍሬና የሰብል ምርት መመረቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የከተማ ግብርና ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ አለማየሁ ታዬ ለዋልታ እንደገለጹት በከተማይቱ አምስት ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ከ3 ሺ በላይ የከተማ አርሶ አደሮች የማዳበሪያ ፤የምርጥ ዘር እና የምክር አገልገሎት ድጋፍ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
ቢሮው በዘንድሮ ዓመት ለፍራፍሬና ለእንስሳት መኖ የሚያገለገሉ 23 ሺ ችግኞችን ለተጠቃሚዎች ማሰራጨቱንም የሥራ ሂደት ባለቤቱ ገልጸዋል፡፡
ለከተማ ግብርና ዘርፍ ይሰጥ የነበረው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር የገለጹት ሃላፊው አሁን ግን ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ ረቂቅ የከተማ ግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ገልጸዋል ፡፡
በአነስተኛና ጥቃቅን ዘረፍ የተሰማሩ ወጣቶች በከብትና ዶሮ እርባታ ፤በፍራፍሬና እንጉዳይ ምርት ለ452 ሰዎች ሥልጠና መሠጠቱንም አቶ አለማየሁ ታዬ ገልጸዋል፡፡
በ2005 የበጀት ዓመት ዘርፉን የበለጠ ለማጠናከር እንዲቻል የ9 ሚሊዮን ብር ባጀት መፈቀዱንም አቶ አለማዮሁ ገልጸዋል፡፡
| < Prev | Next > |
|---|


