ለቴክኒክና የሙያ ትምህርት አሠልጣኞች ሥልጠና ሊሰጥ ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሓምሌ 12/21004 (ዋኢማ) - ለቴክኒክና የሙያ ትምህርት አሠልጣኞች የሙያ ክህሎት ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ወርቁ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ በአሠልጣኞቹ በኩል የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሙላት ለሁሉም የመንግሥት ቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞችን በተያዘው ክረምት ሥልጠና ይሰጣል፡፡

ሥልጠናውን መስጠት ያስፈለገው አብዛኞቹ የዘርፉ ሠልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘና ባለማለፋቸው የአሠልጣኞች የሙያ ክህሎት ክፍተት በመኖሩ ነው፡፡

የሙያ ክህሎት ክፍተት፣ ለሥልጠናው በተዘጋጀው መመሪያ አለመመራት፣ የትብብር ሥልጠናዎችን ለመስጠት የተቋማት ትብብር ማነስ፣ እንዲሁም በቅንጅት አለመሥራት ለአብዛኞች ሠልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘናን አለማለፍ ምክንያት ሆኗል።

አሠልጣኞቹን የሙያ ክፍተታቸውን የሚሞሉበት የክረምት ሥልጠና እንደተዘጋጀ ገልጸው ሥልጠናው በመጪው ዓመት አሠልጣኞች ብቁ የሆነ ሠልጣኝ እንዲያፈሩ ጥሩ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የሚሰጠው ሥልጠና በአነስተኛና ጥቃቅን ማኅበራት ለተደራጁ አካላት በቴክኒክና ሙያ ረገድ ሰፊ የሙያ ድጋፍ ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም አስረድተዋል።

በቴክኒክና ሙያ ውስጥ ላሉ ኃላፊዎች፣ ግንባር ቀደም አሠልጣኞችና ደጋፊ የሥራ ሂደት ኃላፊዎች ግምገማዊ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑንም አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት የከተማዋ የሙያ ብቃትና ማረጋገጫ ማዕከል በሰጠው መግለጫ ከዘንድሮው የመንግሥትና የግል የቴክኒክና የሙያ ሠልጣኝ ተመራቂዎች 29 በመቶ ያህሉ ብቻ ፈተናውን ማለፋቸውን መገለጹ ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results