በጉጂ ዞን በቡና ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶች ከፍተኛ ገቢ አገኙ

  • PDF

አዲስ አበባ፤  ሐምሌ 12/2004 (ዋኢማ) -   ለመጀመሪያ ጊዜ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚበልጥ ገቢ ማግኘታቸውን በጉጂ ዞን በቡና ተክል ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ።

በወረዳው በቡና ልማት ከተሰማሩት አምስት ባለሀብቶቹ መካከል አቶ ዱባ ቁንቢ ፣አቶ ወደሳ ያቺሴ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ምርታቸውን ከማእከላዊ ገበያ በተጨማሪ በቀጥታ ለሲውዲን፣ ጃፓንና አሜሪካ ገበያ በማቅረብ ገቢውን ማግኘት ችለዋል።

በሻኪሶ ወረዳ ከ200 ሔክታር የሚበልጥ መሬት ላይ ያለሙትን ከስምንት ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ምርት ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረባቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ ያቀረቡት ቡና በጥራቱ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ በመውጣት የጥራት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትና ልዩ ሽልማት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ቡናን በብዛትና በጥራት ለገበያ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀው በሚቀጥለው አመትም ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርቡትን ምርት ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለሀብቶቹ ለ500 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ማስገኘታቸውን የጉጂ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማደራጀና ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወልዴ ገብሬ አስታውቀዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ  ባለሀብቶቹ በአምስት ሚሊዮን ብር ካፒታል በማህበር በመደራጀት የኢንቨስትመንት ስራ መጀራቸውንም ገልጸዋል።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 594 guests