የአፍሪካ ትብብር ኢኒሼቲቭ ይፋ ሆነ

  • PDF

አዲስ አበባ ሃምሌ 7/2004/ /ዋኢማ/ -በአህጉሪቱ አፍሪካ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና አህጉሪቱን መልሶ ለመገንባት አቅም ይሆናል የተባለው የአፍሪካ ትብብር ኢኒሼቲቭ ይፋ ተደረገ፡፡

የአፍሪካ  ህብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወያይቶ ይፋ ያደረገው ይህ ትብብር ለአህጉሪቱ  የግጭት አፈታትና ሀገራት በተናጠል ለጀመሩት የዕድገት ጉዞ አጋዥ ይሆናል ነው የተባለው።

አፍሪካ ለአፍሪካ የሚል መርህ ይዞ የተነሳው ይህ ትብብር የአህጉሪቱ ሀገሮች ግጭቶችን በራሳቸው እንዲፈቱ የአቅም ግንባታ ከመፍጠሩም ባሻገር ሀገሮች በትብብር የሚሰሩበትን መንገድ ያመቻቻል ተብሏል።

በግጭት መሰረተ ልማታቸው የወደመባቸው ሀገሮችን መልሶ ለመገንባት የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉና ይህን ትብብር ለማገዝ እንደተዘጋጁም ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የግጭት ሰለባ የሆኑ 6 ሃገሮች ከግጭት እየወጡበት ያለውን መንገድና አሁን ያሳዩትን መሻሻል በሚኒስትሮቻቸው አማካኝነት መብራራቱን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ፣ግብጽ፣ ኬንያና ዩጋንዳ በግጭት አፈታት ዙሪያና ከሀገራት ጋር ተባብሮ በመስራት ያላቸውን ልምድ እና ተሞክሮም አቅርበዋል።

















  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 311 guests