በመላ ሀገሪቱ ከ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል ስራ ተጀምሯል

  • PDF

አዲስ አበባ ሀምሌ 5/2004/ዋኢማ/ - የግብርና ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ ከ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደገለፀው፤ የችግኝ ተከላው የሚከናወነው በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች ነው እየተተከሉ የሚገኙት።
የአፋርና የሱማሌ ክልሎች አብዛኛው አካባቢ ዝናብ የማያገኙ በመሆናቸው ተከላው በሌላ ወቅት እንደሚከናወንም አስረድተዋል።

በዚህ ክረምት ከሚተከለው ችግኝ እስከ 85 በመቶ የሚሆነው እንዲፀድቅ ለማድረግም የተለያዩ ስራዎች ይሰራሉ።

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ደንታሞ እንዳሉት በየአመቱ በዚህ ወቅት በሚከናወን የችግኝ ተከላ ላይ አብዛኛው የከተማና የገጠር ነዋሪ ተሳታፊ ይሆናል።

አብዛኞቹ ሀገር በቀል ችግኞችና ጠቀሜታ ያላቸው ዛፎች ሲሆኑ የመሬት መሸርሸርን በተፈጥሮ መከላከል የሚችሉ ዛፎችና የእንስሳት መኖ በብዛት ይገኙበታል።

በዚህኛው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች በሀምሌ ወር ሙሉ በሙሉ ተተክለው እንዲጠናቁ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም የክረምቱ ዝናብና እርጥበት ለችግኞቹ መፅደቅ ወሳኝ በመሆኑ ነው ብለዋል አቶ ዳንኤል።

ባለፈው ክረምት ከተተከሉት ችግኞች ከ75 በመቶ በላይ መፅድቁን ተናግረው በዚህ ክረምት የሚተከሉት ደግሞ ከዚህ በላይ እንዲፀድቁ የማድረግ ስራ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ባልደረባችን ኤልሳቤት ካሳ ዘገባ ለችግኞቹ ሙሉ ለሙሉ መፅደቅ የህብረሰተቡ እንክብካቤ ወሳኝ በመሆኑ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።



  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 204 guests