የስኳር ፋብሪካዎችን የማስፋፋትና የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

  • PDF

አዲስ አበባ ሰኔ 28/2004/ዋኢማ/ - በ2005 ዓ.ም የእቅድ ዘመን ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ወደ ማምረት የሚሸጋገሩበትና አዳዲሶቹ ፕሮጀክቶች ደግሞ የልማቱን ሥራ አስፋፍተው የሚቀጥሉበት ዓመት እንደሚሆን የስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አባይ ፀሐዬ ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች የኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑ የ2005 ዓ.ም እቅድ ለውይይት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ መጪው ዓመት የአምስት ዓመቱን የልማት እቅድ በስኬት ለማጠናቀቅ እጅግ ወሳኝ ዓመት ነው።

በስኳር ዘርፍ ዕቅድ ሦስተኛ ዓመት የሚሆነው 2005 ዓ.ም ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ወደ ምርት እንደሚሸጋገሩ ጠቁመው፤ በአዳዲሶቹም የልማቱን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግና በማስፋፋት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለፃ፤ ኮርፖሬሽኑ ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ባሳለፋቸው 18 ወራት ከነባሩ አደረጃጀት የተረከባቸውን የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የክህሎትና የሥነ-ምግባር ችግሮችን ለመፍታት ይጥራል።

ኮርፖሬሽኑ በ2005 የልማት ዘመን በፍጥነት ወደምርት ሊገቡ በሚችሉት የጣና በለስ፣ ወልቃይትና የኦሞ፣ ኩራዝ ቁጥር አንድ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ አቶ አባይ ገልጸዋል።
በሌሎችም በአምስት ዓመቱ እቅድ መሠረት እንዲጠናቀቁ ደረጃ በደረጃ የመስኖ መሠረተ ልማት፣ የቤቶች ልማት፣ አገዳ ተክል ልማትና የፋብሪካ ተከላ እንደሚከናወን መናገራቸውንም  ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 307 guests