ኤም አይ ፋይፍ አስቸጋሪ የሆኑ የመረጃ መረቦች ጥቃትን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን ገለጸ

  • PDF

ኤም አይ ፋይፍ በእንግሊዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚፈጸሙትን  የመረጃ መረቦችን  ጥቃት ለመከላከል እየሰራ እንደሚገኝ  የደርጅቱ ዋና ኃላፊ ጆናታን ኢቫንስ  አስታወቁ፡፡

ዋና ኃላፊ በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ኢንተርኔት የሚፈጥረውን የመረጃ ተጋላጭነት እድል በመጠቀም አንዳንድ ወንጀለኞችና መንግሥታት መረጃዎችን ለሚፈልጉት ሥራ እያዋሉት ነው ብለዋል፡፡ 

እንደዚህ አይነት የመሰሉ የመረጃ ላይ ጥቃቶችን መፈጸም የመረጃ ነጻነትን የሚጋፋ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው እንደ ለንደን 2012 ኦሎምፒክ አይነት ዝግጅቶች አሸባሪ ቡደኖች አላማቸውን ለማሳካት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት እንደሚችል  በማስጠንቀቅ የደህንነት ስጋቶችን ለማስወገድ ዝግጅቶ እየተካሄዱ ይገኛሉ ብለዋል።   

እንደ ዋና ኃላፊው ገለጻ የኦሎምፒክ ዝግጅቱ በቀላሉ የሽብርተኞች ኢላማ  እንደማይሆን ገልፀው፤ ሽብርተኞችም የኦሎምፒክ ዝግጅቱን ለማደናቀፍ የተለያዩ ጥረቶች እያደረጉ መሆናቸውንም አንዳንድ ጠቋሚ የሆኑ መረጃ እንዳገኙም ተናግረዋል።

ከመረጃ  መረብ ጥቃቶች  በስተጀርባ  በሺዎች  የሚቆጠሩ ሰዎችና መንግሥታት ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ኃላፊው የተደራጀ የመረጃ ስለላና የጥቃት ወንጀል  በመፈፀም ላይ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ኢንተርኔት በራሱ የሚፈጥረውን የመረጃ ተጋላጭነትን በመጠቀም ወንጀለኞች ብቻ ሳይሆኑ መንግሥታትም ያለ አግባብ የመረጃ ስርቆትን እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ሩሲያና ቻይና በሃገር ደረጃ  በአብዛኛው ጥቃት ከሚሰነዝሩ ሃገራት መካከል እንደሚመደቡ ገልፀው፤ ይህ አድራጎታቸውም የእንግሊዝን መንግስት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የተለያዩ ሀገራትን መረጃ ተአማኒነት፣ ሚስጥራዊነትና በቀላሉ  መረጃን  በማሰራጨት ስጋት ላይ ከመጣላቸውም በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ከንግድ እስከ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ መረጃዎች አደጋ ላይ እንዲወደቁ ያደርጋል በማለት ሚስተር  ኢቫንስ ተናግረዋል፡፡ 

በመሆኑም የጉዳዩ አሳሳቢነት የመንግሥት ሚስጢር  ሊወጣ  ይችላል ብቻ ሳይሆን  የሃገሪቱን የመሠረተ ልማት፣ አዕምሮአዊ ንብረትና አንገብጋቢ የሆኑ የንግድ መረጃዎች አደጋ  ላይ እንዳይወድቁ መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ኦሎምፒክ የአለም አቀፍን ህብረተሰብ ትኩረትን ስለሚስብ የሽብርተኞች ኢላማ ሊሆን ይችላል ያሉት ኃላፊው ነገር ግን ኤም አይ ፋይፍ አርኪ የሆነ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል በማለት ኃላፊው ገልፀዋል። የኦሎምፒክ ጨዋታ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ኤምአይፋይፍ ጽህፈት ቤት ያለምንም እረፍት ስራዎችን እንደሚሰራም ተናግረዋል።