በውጭ አገር የተካሔደው የመማሪያ መጻሕፍት ሕትመትና ዝግጅት ለአገሪቱ ትልቅ ልምድ ያሰገኝ ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2004 (ዋኢማ)- በውጭ አገር የተካሔደው የመማሪያ መጻሕፍት ሕትመትና ዝግጅት ለአገሪቱ ትልቅ ልምድ ያሰገኝ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ግርማ አለማየሁ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቶች ላይ የተደረገው የመማሪያ

መጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ትልቅ አቅምና ልምድ እንድንቀስም አዷርጓል፡፡

መጽሐፍቶቹ የታተሙት በእንግሊዝ ፣ በሕንድና በኡጋንዳ ሲሆን ለዚሁ የመጸሐፍት ሕትመትና ስርጭት 150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ እንደተደረገበት አብራርተዋል፡፡

አለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የልማት አጋሮች በፕሮጀክቱ ውጤታማነት ላይ ምስክርነታቸውን መስጠታቸውንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሕትመት ስራዉ ለአገር ውስጥ ትልቅ አቅምን የፈጠረ መሆኑንና በቀጣይም አገር ውስጥ መፀሐፍቶችን ማዘጋጀትና አትሞ እስከ ማሰራጨት የሚያደርስ ልምድ ለመቅሰም መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ከባለፈው አመት ጀምሮ ከታሪክ መጽሐፍት ውጪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው በአግባቡ መሰራጨታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአንደኛ ደረጃ ትምህርትም እንደዚሁ ካላቸው ባሕርያት የተነሳ ከክልል ክልል የሚለያዩት የአካባቢና የተቀናጀ ሳይንስ መጽሐፍቶች ውጪ ሌሎቹ ተዘጋጅተውና ታትመው መሰራጨታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ከጥቂት ትምህርቶች በስተቀር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የመፀሐፍት እጥረት እንዳይከሰት ሁሉም ክልሎች ወደ ዳግም ሕትመት አንዲገቡ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቀት በመማር መስተማሩ ሒደተ የመጽሐፈት እጥረት እንዳይከሰት መንግስት እየሰራ ሲሆን ከ100 በላይ መጽሐፍቶች በሚኒስቴሩ ድሕረገጽ ላይ ማግኝት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት እንደገጠመው አይነት የመፀሐፍት ችግር እንዳይከሰት በበላይነት እየመራና እየተከታተለ መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ ከክልል ትምህርት ቢሮችም ጋር በዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 200 guests