የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 14ኛ አመት የምስረታ በዓል ዛሬ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2004 (ዋኢማ)- የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት የጀመሩትን የልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከዳር ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ)14ኛ አመት የምስረታ በዓል ዛሬ በሠላማዊ ሠልፍና የባህል ፌስቲቫል በደመቀ ስነ ስርዓት በጅጅጋ ከተማ ተከበሯል፡፡
በአሉ በጅጅጋ ከተማ ስታዲዮም ሲከበር የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበርና የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር እንደገለጹት ፓርቲው የነደፋቸው ፈጣን የአርብቶ አደር ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማሳካት ባለፈው አመት የጀመረው የህዳሴ መስመር ውጤታማ ሆኗል፡፡
የክልሉ መንግስትና ህዝብ የጀመሯቸው የልማት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግር ከማቃለል አልፎ በርካታ የውጪና የሀገር ወስጥ ባለሀብቶችን ወደ ክልሉ መሳብ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ አብዲ ይህን ለውጥ ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ፓርቲው በክልሉ በሚሰጠው አመራር በሁሉም የልማት መስኮች የተሻለ ለውጥ እየታየ መሆኑን ገልጸው በውሃ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ስራ ላይ ያለውን ችግር ለማቃለል ፓርቲው ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሳዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ መሀመድ ረሼድ ኢሳቅ በበኩላቸው በክልሉ የነበረውን ጎሰኝነትና የጠባብ አመለካከት ችግር በማስወገድ በዞኖችና ወረዳዎች መልካም አስተዳደር ለማስፈን መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ከ240 ሺህ የሚበልጡ የፓርቲው አባላት በየአከባቢያቸው በሚካሄዱ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
በዓሉ በቱሌ ጉሌድ ወረዳ በሠላማዊ ሠልፍና በውይይት መከበሩን የገለጹት የወረዳው የፓርቲ ጉዳዩች ኃላፊ አቶ መሀመድ ኢድ ናቸው፡፡
በጅጅጋ ከተማ በተካሄደ የሻማ ማብራት ስነስርዓትና የባህል ፌስቲቫል ላይ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተክለብርሃንና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ በጅጅጋ ከተማ ከሚገኙ ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች፣ የቢሮ ኃላፊዎችና ከዘጠኝ ዞኖች የተወከሉ የባህል ፌስቲቫል አቅራቢዎች መሳተፋቸውን ኢዜ አ ዘግቧል ፡፡
ክሱን ሲመረምር የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ካላቸው መካከል 8ቱ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 12 ቱ ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለመኖራቸው በሌሉበት የጥፋተኛነት ውሳኔ ተላልፎባቸል፡፡
የጥፋት ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ዮሐንስ ተረፈ፣ የሽዋስ ይሁንዓለም፣ ክንፈሚካኤል ደበበ፣ ምትኩ ዳምጤ፣ እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አያሌው በማረሚያ ቤቱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሌሉበት ከተከሰሱት መካከል ዶክተር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይገኙበታል፡፡
በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የተከፈተው በ24 ግለሰቦች ላይ የነበረ ሲሆን አራቱ ቀደም ሲል በታዩት ችሎቶች ከጥፋተኝነት ነጻ ሆነው በመገኘታቸው የተለቀቁ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
| < Prev | Next > |
|---|


