18 May 2013
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን እያደረገች ያለውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20 /2004 (ዋኢማ) - ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን እያደረገች ያለውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ፡፡
በሶማሊያ እየታየ ላለው የሰላም ሁኔታ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ ግንባር ቀደም ሚና እንዳለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጽህፈት ቤታቸው ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ከሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ ጋር በሶማሊያ ስላለው ሁኔታ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት የሶማሊያ ሰላምና ጸጥታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የሶማሊያ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን የአፍሪካ አገራት በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ በአንድ ድምፅ እየሰሩ መሆናቸውንም ያመላከተ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ በበኩላቸው በሽግግር ዘመን ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ በአገሪቱ በተሻለ ሁኔታ ሰላምን ለማስፈን እየተሠራ እንደሆነ መገንዘባቸውን እንደተናገሩ ኢ ዜ አ ዘግቧል፡፡
| < Prev | Next > |
|---|


